የደብረ ታቦር በዓል በሄልሲንኪ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከበረ
by ግንኙነት ክፍል
በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የደብረ ታቦር በዓል የደብሩ ሕጻናት አዳጊ ልጆች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል ።
የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይሜኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ በበዓሉ ላይ እንደተናገሩት በተለይ በዝርወቱ ዓለም ተወልደው የሚያድጉ ተተኪው ትውልድ የበዓላትን አከባበር እንዲሁም ትውፊታዊውንም ቅብብል በተግባር ያውቁ ዘንድ እንዲያስችል ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። ወላጆችም ለዚሁ ትልቅ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ ብለዋል ። በቀጣይ የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ አዲስ ዓመትም እንዲሁ በደሜቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚከበር ጠቁመዋል።
በተያያዘ ዜና ነሐሴ 14 /2014 ዓ.ም በታምፔሬ ከተማ በታምፔሬ የሚገኙ የቅድስት ኪዳነ ምሕረት ጽዋዕ ማኅበር አባላት አዘጋጅነት የፍልሠታ ለማርያምን በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ መርሐ ግብር ተዘጋጀ ።
በታምፔሬ የፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በጸሎተ ቅዳሴ የተጀመረው መርሐግብሩ ትምህርተ ወንጌልም የተሰጠ ሲሆን በሄልሲንኪ ደብረ አሚን ጽጌ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት መዘምራን ወርብ የቀረበ ሲሆን በሕጻናት መዘምራንም እንዲሁ መዝሙር ቀርቧል።
በእለቱም ለረጅም ዓመት በኢትዮጵያ ሲያገለግሉ የቆዩት በታምፔሬ ተወላጅ የሆኑት እና ቀጣይ ኑሮአቸውን በታምፔሬ ለማድረግ የመጡት አቶ አርቶ ስመ ጥምቀቱ (ኃብተ ሥላሴ )እስከነ ቤተሰቦቻቸው እንኳን በሰላም መጣችሁ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ነሐሴ 7/2)14 ዓ.ም ተመሳሳይ መርሐ ግብር በቫሳ ቅዱስ ገብርኤል የጽዋዕ ማኅበር አዘጋጅነት መከናወኑ ይታወሳል።
Recommended Posts
ማኅሌተ ጽጌ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተመረቀ
October 04, 2023
ሀገረ ስብከቱ የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸም ጠቅላላ ጉባኤውን አጠናቀቀ
September 03, 2023
በፊንላንድ ሀገር የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቡራኬ ተከናወነ !
September 03, 2023