የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቫሳ ከተማ ተከበረ
by ግንኙነት ክፍል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የቤተክርስቲያን ሰሜን ምዕራብ አውሮፖ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ቫሳ ከተማ የሚኖሩ ምእመናን ባቋቋሙት የቅዱስ ገብርኤል ጽዋዕ ማኅበር አስተባባሪነት ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በዓል ባሳለፍነው ቅዳሜ ታኅሣሥ 14 ቀን 2010 ዓ.ም በሥርዓተ ቅዳሴና በጉባኤ ተከብሮ ውሏል። በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የሚያገለግሉ ካህናት፤ እንዲሁም ከደብሩ መዘምራን የተወሰኑት ለዚሁ አገልግሎት ከአርብ ጃምሮ በቦታው በመድረስ ቫሳ በሚገኘው የፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለምእመናኑ ቅዳሴ ትምህርትና ምክር አገልግሎት ተሰጥቷል። በተለይም ከቅዳሴው በኋላ በተካሄደው ጉባኤ ላይ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ በዓሉን የተመለከተና ከምእመናን ሕይወት ጋር በማያያዝ ሰፋ ያለና መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሕይወትን የሚያጠነክር ሰፋ ያለ ትምህርትና አባታዊ ምክር ሰጥተዋል። በጉዞው የተሳተፉ የመዝሙር ክፍል አባላትም የዝማሬ አገልግሎት አበርክተዋል። በመጨረሻም መዝሙር ከተዘመረና የመዝጊያ ጸሎት ከተደረገ በኋላ የበዓሉ ፍፃሜ ሆኗል። የቫሳ ከተማ ከሄልሲንኪ 423 ኪሎሜትር ያህል የምትርቅ መሆኗ ይታወቃል ።
የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቫሳ
Recommended Posts
ማኅሌተ ጽጌ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተመረቀ
October 04, 2023
ሀገረ ስብከቱ የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸም ጠቅላላ ጉባኤውን አጠናቀቀ
September 03, 2023
በፊንላንድ ሀገር የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቡራኬ ተከናወነ !
September 03, 2023
እግዚአብሔር ይመስገን
አሜን