የልደትን በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ የሕጻናት መርሐ ግብር ተካሄደ።

የልደትን በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ የሕጻናት መርሐ ግብር ተካሄደ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል የሕፃናትና  አዳጊ ንዑስ ክፍል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ እሑድ ታኅሣሥ 30 ቀን 2009 ዓ.ም (January 8, 2017) ከሰዓት በኋላ ልዩ የሕጻናት እና የአዳጊ ልጆች መርሐ ግብር ተካሄደ።
በመርሐ ግብሩ መጀመሪያ ላይ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ በተላለፈው መልእክት ሕፃናትና  አዳጊ ልጆች የነገ የቤተ ክርስቲያናችን ተረካቢዎች በመሆናቸው  ትኩረት፣ ፍቅርንና ጊዜን ሰጥተን መሥራት የሚጠበቅብን መሆኑን እና ጥሩ ምሳሌ መሆን ከሁሉም ምእመናን የሚጠበቅ መሆኑ ተገልጿል። ይህን መሰል ልዩ መርሐ ግብር ለልጆች ሲዘጋጅ ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ ሲሆን በቤተ ክርስቲያኗ በጀት ስጦታ ሲዘጋጅ ግን ይህ ለ2ኛ ጊዜ እንደሆነ የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍሉ ገልጿል።በዕለቱ የተለያዩ መርሐ ግብራት የቀረቡ ሲሆን ሕፃናትና አዳጊ ልጆች ልደትን አስመልክተው የተለያዩ ዝግጅቶቻቸውን አቅርበዋል። በልጆቹ ከቀረቡት መካከልም፡

  • የጌታ መወለድን የሚያስተምር ሥነ-ጽሑፍ
  • የተለያዩ የልደት መዝሙራት
  • የጥያቄና መልስ ውድድር
  • ወረብ

በመጨረሻ  የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ  ከቤተ ክርስቲያኑ  የተዘጋጀውን ስጦታ ለሕጻናትና አዳጊ ልጆች አበርክተዋል። አስተዳዳሪው ባስተላለፉት መልእክት ”ሕፃናት የእግዚአብሔር ሥጦታዎች ናቸው” መዝ. 126(127)፥3 የሚለውን የመጽሐፍ ቃል መነሻ አድርገው ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሳያቋርጡ እንዲያመጧቸው አጥብቀው መልእክታቸውን አስተላልፈው የመርሐ ግብሩ ፍፃሜ ሆኗል።

የሕጻናት የልደትን በዓል መርሐ ግብር 2009

share

Comments

  1. እመቤታችን እናታችን : January 25, 2017 at 5:39 pm

    እግዚአብሔር ያሳድጋችው በፀጋ በጤና ይጠቃችው

  2. Gebermicheal Redieat : January 25, 2017 at 5:43 pm

    Edegulign tsegawin yabzalachihu! Betam dess yilal bertulin.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *