“ኢትዮጵያ ዛሬ” በሚል መሪ ቃል ዐውደ ጥናት ተካሄደ
by ግንኙነት ክፍል
ነሐሴ 21 2008 ዓ.ም. (27.08.16 እ.ኤ.አ) በሶፈያ የባህል ማዕከል ”ኢትዮጵያ ዛሬ (Etiopia tänään)” በሚል መሪ ቃል በሶፍያ የባህል ማዕከል እና በፊኒሽ ኦርቶዶክስ አስተባባሪነት የተዘጋጀ ዐውደ ጥናት ተካሄደ። ዐውደ ጥናቱ የተለያዩ መርሀግብሮችን በማካተት ከቀኑ 12፡00 እስከ 18፡00 ቀጥሎ ውሏል። ከቀኑ 12-14 ሰዓት በዕለቱ በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጋባዥነት ከስዊድን የሉንድ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መምህር ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ታሪክ በሚመለከት ጥናታዊ ጽሑፍ በማቅረብ ፣ በቦታው ለታደሙት የጉባኤው ተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ግንዛቤ አስጨብጠዋል፡፡ በማስከተልም። ወ/ሪት ፌቨን ትዕግሥቱ “ቱሪዝም በኢትዮጵያ” በተሰኘ ርዕስ የኢትዮጵያን ዋና ዋና የቱሪዝም መስህቦችን አስተዋውቃለች። በዕለቱ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ የተክለሃይማኖት ደብር ሰንበት ት/ቤት መዘምራን ወረብ እና መዝሙር ያቀረቡ ሲሆን፣ በዝግጅቱ ላይ በደብሩ ልማት ክፍል ተዘጋጅተው የቀረቡ የተለያዩ የኢትዮጵያ የባህል ምግቦች እና መጠጦች ለታዳሚው ቀርበዋል።
ኢትዮጵያ ዛሬ
Recommended Posts
ማኅሌተ ጽጌ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተመረቀ
October 04, 2023
ሀገረ ስብከቱ የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸም ጠቅላላ ጉባኤውን አጠናቀቀ
September 03, 2023
በፊንላንድ ሀገር የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቡራኬ ተከናወነ !
September 03, 2023