አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ እረፍት የዋዜማ በዓል በድምቀት ተከበረ!

አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ እረፍት የዋዜማ በዓል በድምቀት ተከበረ!

በፊላንድ ሄልሲንኪ አሉንኩላን ቤተክርስቲያን የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ እረፍታቸውን አስመልክቶ የዋዜማ ጉባኤ የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ ፤ ተጋባዥ እንግዶች መምህር ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ(ከስዊድን) ሊቀ መዘምራን ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ(ከኢትዮጵያ) መምህር ፍቃዱ ሣህሌ(ከኢትዮጵያ) ፣ የሰንበት ት/ቤቱ መዘምህራን እና ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ስነ-ስርዓት ተከብሯል፡፡ ሕጻናትም በፕሮግራሙ ላይ ዝማሬን አቅርበዋል።
በነገውም ዕለት ከቀኑ 12:00 ሰዓት እስከ 18:00 ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 22:00 ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ የአዳር መንፈሳዊ አገልግሎቶች በሶፊያ የባህል አዳራሽ እንደሚቀጥልም ተገልጾዋል። በዋዜማ ሌሊቱን በማህሌት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን በጋራ በመሆን መንፈሳዊ አገልግሎት ይቀጥላል።

ነሐሴ ተክልዬ ንግስ

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *