ቤተ ክርስቲያናች በዛሬው ዕለት አዲስ ድረ ገጽ አስመረቀች

ቤተ ክርስቲያናች በዛሬው ዕለት አዲስ ድረ ገጽ  አስመረቀች

የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክርለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት አዲስ ድረ ገጽ  አስመረቀች። በድረ ገጽ ስም www.teklehaymanot.fi በመባል የተሰየመውን ድረ ገጽ መርቀ የከፈቱት የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ ሲሆኑ የተሠራው ሥራ እጅግ ዘመናዊና ሁሉን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ ለምረቃ የበቃው ድረ ገጽ የተሰራው በቤተ ክርስቲያኗ መረጃና ግንኙነት ክፍል ሲሆን እስካሁን የአራት ወር ጊዜ እንደፈጀ ታውቋል። በአሁን ሰዓት ገጹ ላይም የዜና እና መርሐ ግብር፣ የህብር ሚዲያ፣ የህጻናት፣ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ስርዓተ ቤተክርስቲያን እና ሌሎች አምዶች አሉት። በምረቃው ላይ ስለ ድረ ገጽ ትንታኔ የሰጠው የመረጃና ግንኙነት ክፍል አገልጋይ ወንድማችን ካቢናድ ተሻገር እንደተናገረ ይህ የድረ ገጽ ፕሮጀክት በሶስት ምዕራፍ የተከፈለው ሲሆን ዛሬ ለምረቃ የበቃው የመጀመሪያ ምዕራፍ መጠናቀቅ ተከትሎ ነው። በሁለተኛው ምዕራፍ ስራ የጎደሉ መረጃዎች ተሟልተው የሚቀርብበት፣ ቤተ መጻሕፍት እና የንዑሳን ክፍሎችን አምድ የሚካተትበት፣ እንዲሁም ሙሉ ለሙሉ ወደ አማርኛ ቋንቋ የሚቀየርበት እንደሆነ ተነግሯል። በመጨረሻውም ምዕራፍ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ከተቻለ የፊኒሽኛ ቋንቋ ገጽ እንዲኖረው እንደታቀደ ተገልጿል።

ይህ ለምረቃ የበቃው ድረ ገጽ ለቤተ ክርስቲያኗ ትልቅ የዲጂታል መረጃ ማዕደር እንደሚሆን ሲታመን ቤተ ክርስቲያኗ የምታቀርበውን መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚያሳውቅ እና መረጃዎች ለምዕመኑ በተሻለ ለማድረስ እንደሚያግዝ ይታመናል። ምዕመናንም ባዩት ስራ መደሰታቸውን ሲናገሩ ሁላችንም በሙያችን አስተዋጾ ካደረግን ቤተ ክርስቲያኗን ከዚም በላይ ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸዋል።

በመጨረሻም ምዕመናን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑና ወደ እግዚያብሔር ቤት መጥተው የአገልግሎቱ ተካፋይ እንዲሆኑ መንፈሳዊ ጥሪ ቤተ ክርስቲያኗ አስተላልፋለች ።

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *