በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጽጌ ሃይማኖት ስንበት ት/ቤት ለተተኪ መዘምራን ሥልጠና ተሰጠ

ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም፥ በስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለጽጌ ሃይማኖት ስንበት ትምህርት ቤት ተተኪ መዘምራን ‹‹ ብላቴናነትን የመቀደስ ጥበብ በቤተ ክርስቲያን ›› በሚል ርእስ በመምህር ታደሰ ወርቁ ሥልጠና ተስጥቷል። ሥልጠናውን የወሰዶት አብዛኛዎቹ ብላቴናዎች በፊንላንድ ተወልደው የአደጉ ናቸው ።

በዚህም የሥልጠና ርእሰ ጉዳይ የብላቴናነትና ብላቴናነትን የመቀደስ ምንነት፣ ብላቴናነትን የመቀደስ ጥበብ ምን ምን እንደሆነ ተዳስሷል። የደብሩም ተተኪ መዘምራን ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን አንስተው፤ ለተነሱት ጥያቄዎች በአሥልጣኙና በደብሩ አስተዳዳሪ ሰፊ ማብራሪያይና መልስ ተስጥቷል።

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *