በፊንላንድ ሂልስንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ፈተና ታሳቢ ያደረገ ሥልጠና ተሰጠ
ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም፥ በስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ውቅታዊ ፈተና ታሳቢ ያደረገ ሥልጣን ተካሂዷል።
በሥልጠናው መርሐ ግብር ‹‹ የመንፊሳዊ አገልጋዮች ሡታፌ በዘመነ ቀውስ ›› በሚል ርእስ÷በስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሰብሳቢነት፤ በመምህር ታደሰ ወርቁ ለሰበካ ጉባኤ አባላት፣ ለልዩ ልዩ ክፍል ሐላፊዎችና ለንዑስ ክፍል ተጠሪዎች በአካልና በበየነ መረብ ሥልጠና ተሰጥቷል።
በዚህም ሥልጠና የመንፈሳዊ አገልጋዮች ለአገልግሎት የመታጨት ሂደቶች፣ በአሁን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን የገጠማት ቀውስ ምንነት፣ የዘመነ ቀውስ አገልጋይነት ባሕርያት ምን ምን እንደሆኑ፣ የቀውስ ዘመን አገልጋዮች ሊታጠቋቸውና ሊያጸኗቸው የሚገቡ የአገልግሎት መንፈሳዊ መሣሪያዎች ተዳስሰዋል።
የሥልጠና መርሐ ግብሩን በፊንላንድ ሄልስንኪ የደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጽ/ቤት የተዘጋጀ ሲሆን፤ መርሐግብሩም በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅና በደብሩ አስተዳዳሪ ቃል ምዕዳንና የቀጣይ የሥራ አቅጣጫ ስጪነት መጠናቀቁን በዜናው ተመልክቷል። ተመሳሳይ ሥልጠናዎች ወደ ፊትም እንደሚቀጥሉ ተጠቅሷል።
Recommended Posts
ማኅሌተ ጽጌ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተመረቀ
October 04, 2023
ሀገረ ስብከቱ የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸም ጠቅላላ ጉባኤውን አጠናቀቀ
September 03, 2023
በፊንላንድ ሀገር የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቡራኬ ተከናወነ !
September 03, 2023
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችንን ይጠብቅልን ያብዛን።