በፊንላንድ ሀገር የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቡራኬ ተከናወነ !

በፊንላንድ ሀገር የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቡራኬ ተከናወነ !

ነሐሴ 24 ቀን 2015
+++
ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስዊድን፣ ስካንድንቪያን እና ግሪክ ሀገሮች ሊቀ ጳጳስ በሀገረ ፊንላንድ ዋና ከተማ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ባርከዋል።

የሄልሊንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በ2004 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ እንጦንስ ተባርኮ አገልግሎቱን የጀመረው እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። አጥቢያው እስከ አሁን ድረስ ከፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በውሰት በሚያገኘው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ላይ በወር ሁለት ጊዜ እና በዐበይት በላይ ጊዜ ብቻ አገልግሎት እየሰጠ መቆየቱን ተገልጿል። በአሁን ጊዜ የሕጻናት እና አዳጊ ልጆች እንዲሁም የምዕመንናን ቁጥር እየተበራከተ በመምጣቱ የተነሳ፤ በየዕለቱ ምዕመናን እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት እና የሚለምኑበት፤ እንዲሁም አዳጊ ልጆች በሰፊው ለማስተማር ይሆን ዘንድ ቋሚ የመገልገያ ቦታ መከራየት እንዳስፈለገው የስዊድን፣ ስካንድንቪያን እና ግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አሥኪያጅ እና የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ለማ በሱፍቃድ ገልጸዋል።

የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በመላው ፊንላንድ ላሉ ምእመናን አገልግሎቱን በመፈጸም ረገድ የሚያደርገው እንቅስቃሴም የሚመሰገንና ከአጥቢያው መንፈሳዊ አገልግሎት ያገኙ በርካታ ምእመናንን ሀሳባቸውን ገልጸዋል።

ከዚሁ በተያያዘ ብፁዕነታቸው በዕለቱ በደብሩ ሲያገለግሉ ለነበሩ ሁለት ዲያቆናት የቅስና ማዕረግ እንዲሁም ለሦስት የአብነት ተማሪዎች የዲቁና ማዕረግ ሰጥተዋል። አዲሱን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ባርከው የከፈቱት እና ሲመተ ክህነቱን የሰጡት አንጋፋው አባት ብፁዕ አቡነ ኤልያስም ደብሩ የበለጠ ሊጠናከር እና በአጭር ጊዜ ውስጥ የራሱ የሆነ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን መግዛት እንደሚገባ በማሳሰብ ተተኪ አገልጋይ መሆን የሚችሉ ዘመኑን የዋጁ አገልጋዮችን የማፍራቱን ሂደትም አጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *