በዓለ ጥምቀት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

በዓለ ጥምቀት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጥር 13 ቀን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት ቲኩሪላ በሚገኘው በፊኒሽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

በዕለቱ በተያዘው መርሃ ግብር መሠረት ሥርዓተ ቅዳሴው ከተከናወነ በኋላ የባህረ ጥምቀቱ ሥርዓተ ጸሎት ተደርሶ ህዝቡም ጸበል ተረጭቶ የበረከቱ ተካፋይ ሆኗል፡፡በመቀጠልም በደብሩ መዘምራን ዕለቱን የተመለከተ  ያሬዳዊ ዜማ የቀረበ ሲሆን  በመጨረሻም በደብሩ አስተዳዳሪ በመጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ   ትምህርተ  ወንጌል  እና ጸሎተ ቡራኬ ከተሰጠ በኋላ  የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

ጥምቀት በዓል አከባበር 2009

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *