በሄልሲንኪ ከተማ አውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው

by ግንኙነት ክፍል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን “የእናት ቤተ ክርስቲያናችንን አደራ እንጠብቅ አንድነታችንንም አንተው” በሚል መሪ ቃል ልዩ የአውደ ርዕይ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚያካሄድ አስታወቀ። ግንቦት 12 2008 ዓም በሄልሲንኪ ከተማ ይካሄዳል የተባለው መርሐ ግብር አላማው የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና እንዲኖረው ማድረግ። ወደፊት ስለ ተረካቢ ህፃናትና ከፊንላንድ መንግስትና ለሚመለከታቸው ግንዛቤ መፍጠር በፊንላንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አመሰራረት ታሪክና ዛሬ ያለንበትን ደረጃ ማስተዋወቅ ናቸው። በዝግጅቱ ላይ ከተለያዩ ቤተ እምነቶች ከመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንግዶች ይጋበዛሉ።አውደ ርዕዩ ከቤተ ክርስቲያኗ 5ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ጋር በጋራ ይከበራል።
Recommended Posts
በፊንላንድ ዩቫስኲላ ከተማ የቅዱስ ዑራኤል ጽዋዕ ማኅበር ተመሠረተ።
March 11, 2023