ቅዱስ ሲኖዶስ በውጭ በሚገኘው ሲኖዶስ ላይ አሳልፎ የነበረውን ቃለ ውግዘት አነሳ

  • የተላኩብፁዓን አባቶች፣የተደረሰበትን ስምምነት የሚያስረዳ መግለጫ ለጉባኤው አቀረቡ፤
  • የነበረው የአባቶች መለያየት ለውግዘት በሚዳርግ ደረጃ ላይ ደርሶ እንደነበር የታወቀ ነው፤
  • የተደከመበት ዕርቀ ሰላም ለውጤት በመብቃቱ በስምምነቱ መሠረት ውግዘቱ ተነሥቶአል፤
  • የጳጉሜ 1984፣ የመስከረም 1985፣ የጥር 1999ዓ.ም.ቃለ ውግዘት፣ከዛሬ ጀምሮ ተነሥቶአል
  • ከልዩነት በፊት የተሾሙ ነባር ሊቃነ ጳጳሳትንና ከልዩነት በኋላ የተሾሙትን ተቀብሏቸዋል፤

†††

  • ስያሜያቸው እንዳለ እንደተጠበቀ፣በውጭ ሀገርም ኾነ በሀገር ቤት ተመድበው ያገለግላሉ፤
  • ከ1-6 ተራቁጥር የተዘረዘሩትን የዕርቀ ሰላም ነጥቦች ምልዓተ ጉባኤው ተቀብሎ አጽድቋል፤
  • የቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና የሀገር ሰላም የበለጠ እንዲጠናከር የበኩሉን ይፈጽማል፤
  • ጠ/ሚሩ፣ ችግሩ የሀገርም መኾኑን በመገንዘብ አስተጋባኢና አሰባሳቢ መመሪያ ሰጥተዋል፤
  • ብዙ የተደከመበት ጉዳይ ፈጣን መፍትሔ እንዲያገኝ ስላደረጉ ልባዊ ምስጋና ያቀርባል::

†††

ምንጭ: ሐራ ዘተዋሕዶ

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *