ለቀጣይ ሁለት ዓመታት የሚያገለግሉ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት ምርጫ ተካሄደ ።

ለቀጣይ ሁለት ዓመታት የሚያገለግሉ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት ምርጫ ተካሄደ ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድንና ስካንድኔቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ቤተክርስቲያን እሑድ ታኅሣሥ 11 ቀን /2013 (20.12.2020) በርቀት በስካይፔ ባካሄደው ዓመታዊ የአጥቢያ ምእመናን መንፈሳዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፈረንጆቹ ከ2021 ዓ.ም ጀምሮ በደብሩ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ቤተክርስቲያኗን የሚያገለግሉ አዲስ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላ ምርጫን አካሄዷል። ጠቅላላ ጉባኤውን በጸሎት ክፍተው የመሩት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ የዕለቱን አጀንዳዎች ማለትም

  •  የደብሩን የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ነጥቦች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ
  •  የ2021 በጀት ዓመት ማጽደቅ
  •  የሰበካ ጉባኤ ምርጫ

ማከናወን መሆናቸውን ገልጠዋል ።
የጠቅላላ ጉባኤ የምርጫው ሂደት ከመናወኑ በፊት የተሻሻሉት የደብሩ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ላይ ውይይት ተደርጎ የማጽደቅ ሂደት እና እንዲሁም የ2021 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ከተደረገ በኋላ ጽድቋ።
እንደሚታወሰው ከሁለት ሳምንት በፊት የሰበካ ጉባኤ የምርጫ ሂደቱ ለማከናወን የደብሩ ምእመናን የተሳተፉበት ሦስት የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት ምርጫ መካሄዱ አይዘነጋም ።
የአስመራጭ ኮሚቴም ከምእመኑ በጥቆማ እጩዎችን የተቀበለ ሲሆን ቃለ ዓዋዲውን መሠረት በማድረግ ስምንት ዕጩዎችን ለጠቅላላ ጉባዔው አቅርቦ አራቱን አባላት ጠቅላላ ጉባኤው መርጠዋል።
በጠቅላላ ጉባዔው መንፈሳዊ የምርጫ ሂደት መሠረት ተመራጮቹ ለቃጣዮቹ ሁለት ዓመታት የሄልስንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉ ሲሆን

  1. ዶ/ር በኃይሉ ሽፈራው
  2. ወ/ት ማርታ በላይ
  3. አቶ ፍጹም ተስፋዬ
  4. አቶ ዳንኤል መኮንን

መመረጣቸው ታወቋል።
በመጨረሻም የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ ተመራጮቹ የሰበካ ጉባኤ አባላቱ ቤተ የአጥቢያ ክርስቲያናችንን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የማስተባበር ከፍተኛ ሓላፊነት እንዳለባቸው ጠቅሰው የሁሉም ሕዝበ ክርስቲያን ትብብር እንደሚያስፈልግም መልእክት ካስተላለፉ በኋላ ጉባኤው በጸሎት ተዘግቷል።

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *