የ፳፻፲፭ ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በሄልሲንኪ ፊንላንድ በደማቅ ሥነሥርዓት ተከበረ

by ግንኙነት ክፍል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሄልሲንኪ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ማርያም አቢያተ ክርስቲያን በአንድነት የመስቀልን ደመራ በዓል በደማቅ ሥነ ሥርዓት አከበሩ።
በዕለቱ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ካህናት እና ምእመናን ከመላዋ ፊንላንድ የመጡ በአንድነት በቦታው ተገኝተዋል።በተጨማሪም በክብር እንግድነትም የሂልሲንኪ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሊዮ ዋና ፀሐፊ ቀሲስ ላዛርዩስ ተገኝተው ለሕዝበ ክርስቲያኑ መልእክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም የሁለቱ አድባራት አስተዳዳሪዎች ፣መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድና ሊቀ ብርሃናት ቀሲስ አንገሶም ዕቁባይ ትምህርት ከሰጡ በኋላ ደመራው ተለኩሶ ሕዝበ ክርስቲያኑ በጋራ ዝማሬ ዘምረው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኖአል።
Recommended Posts
በፊንላንድ ዩቫስኲላ ከተማ የቅዱስ ዑራኤል ጽዋዕ ማኅበር ተመሠረተ።
March 11, 2023