ከ2019 – 2020 ዓ.ም የሚያገለግሉ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት ምርጫ ተካሄደ፡፡

የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለቀጣይ ሁለት ዓመታትየሚያገለግሉ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት ምርጫ አካሄደ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን  አውሮጳ በስዊድንና አካባቢው ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 7 ቀን 2011 ዓ.ም (16.12.2018 ) ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ከ2019  – 2020 ዓ.ም የሚያገለግሉ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤአባላት ምርጫ አካሄዷል፡፡ለሁለት ዓመታት በሰበካ ጉባኤ አባልነት የሚያገለግሉ አባላትን ለመምረጥ ጥቅምት 24 ቀን 2011 ዓ.ም (3.11.2018) በአጥቢያው ምእመን ሶስት አባላት ያለው የአስመራጭ ኮሚቴ  ተመርጦ የምርጫ ሂደቱን ተከናውኗል።

በሐምሌ ወር 2010 ዓ•ም በአስተዳደር ለሁለት ተከፍሎ የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስን አንድነትን ተከትሎ በፊንላንድ ሄልሲንኪም ተግባራዊ የሆነው የምእመናንን አንድነትን ያካተተ የሰበካ ጉባኤ ምርጫ እንዲከናወን የሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በአስተላለፉት መመሪያ መሠረት በከተማው ካሉት ምእመናንን ያካተተ   በአጠቃላይ 24 ዕጩዎች ለጥቆማው የቀረቡ ሲሆን፤ የአስመራጭ ኮሚቴው ቃለ አዋዲውን መሠረት በማድረግ  ዕጩዎቹን ለጠቅላላ ገባኤው አቅርቦ ስድስት አአባላት ለሰበካ ጉባኤ አባልነት ተመርጠዋል በዚሁ መሠረት

  1. ሊቀ ዲን. እሸቴ ተስፋዬ
  2. አቶ ታዬ ነጋሽ
  3. ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ ዮሐንስ
  4. አቶ ካቢናድ ተሻገር
  5. አቶ አማኑኤል ከበደ
  6. ወ/ሮ መቅደስ ፈለቀ የተመረጡ ሲሆን የደብሩ አስተዳዳሪን ጨምሮ ሰባት አባላት ሆነው አገልግሎትን የሚቀጥሉ ይሆናል  ።

በተያያዘ ከአንድ ወር በኋላ ነባሩ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የ2018 ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የሒሳብ ሪፖርት እንዲሁም የ2019 ዓመት ዕቅድ  አቅርቦ አገልግሎቱን እንደሚያጠናቅቅ ታውቋል።

አዲስ ለተመረጡ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን።

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *