የሀገረ ስብከት ምሥረታ ተከናወነ

የሀገረ ስብከት ምሥረታ ተከናወነ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን አውሮጳ መንበረ ጵጵስናው ስዊድን ስቶኮሆልም የሆነ ሀገረ ስብከት ተመሠረተ ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት አሠርተ ዓመታት ያህል በአስተዳደር ተከፍላ ብትቆይም በሐምሌ 2010 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሕደቱ ከተፈጸመ በኋላ በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት አውሮጳን ለዐራት አህጉረ ስብከት እንዲከፈል መወሰኑ ይታወቃል ። በዚህ መሠረት በስዊድንና እስካንድንቢያን ሀገሮች እራሱን ችሎ አንድ ሀገረ ስብከት እንዲሆንና በአንጋፋው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ እንዲመራ በመወሰን የተነሳ መጋቢት 6 እና 7 /2011 ዓ.ም በመንበረ ጵጵስናው ስቶኮሆልም ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ሰብሳቢነት ምሥረታው ተከናውኗል ።በዕለቱም በተያዘው አጀንዳ መሠረት የተለያዩ ውሳኔዎች የተወሰኑ ሲሆን የሀገረ ስብከቱም ሥራ አስፈጻሚ አባላትም ተመርጠዋል ። በስብሰባውም ቤተ ክርስቲያን ለመትከል የሚያስፈልጉ መስፈርቶች ምን እንደሆኑ : በምእመናን መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ችግሮችን ስለመፍታትና የመሳሰሉትን በአጽንኦት ተነስቶ ውሳኔ የተላለፈባቸው ሲሆን ብፁዕነታቸውም አጽንኦት ሰጥተውበታል ። በስብሰባውም ላይብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የጣልያንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ጳጳስ : የአድባራት አስተዳዳሪዎች የምእመናን ተወካዮች ተገኝተዋል።

በመጨረሻም የሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ቀጣዩ የአገልግሎት ዘመን ከዚህ በፊት የንደነበረው ሳይሆን የተሻለ እና ውጤታማ የአገልግሎት ዘመን ይሆን ዘንድ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፈዋል ።በተያያዘ ሀገረ ስብከቱ ለአገልግሎት ያመች ዘንድ በሦስት ቀጠናዎች የተከፋፈለ ሲሆን ኖርዌይ ያሉ አቢያተ ክርስቲያናት : ስቶኮልሆም እና ፊንላንድ ያሉ አቢያተ ክርስቲያናት :እንዲሁም ጉተንበርግ :ሉንድና ኮፕንሀገን ያሉ አቢያተ ክርስቲያናት ናቸው። የሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በቅርቡ ለሦስቱም አቅጣጫዎች አስተባባሪዎች / ሊቃነ ካህናት እንደሚመደብ ታውቋል።

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *