በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር የአንድ ቀን ዐውደ ርእይ ተካሄደ

በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር የአንድ ቀን ዐውደ ርእይ ተካሄደ

በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር ግንቦት 13/2008 ዓ.ም (May 21 2016) “የእናት ቤተ ክርስቲያናችንን አደራ እንጠብቅ አንድነታችንንም አንተው” በሚል መሪ ቃል ልዩ የአንድ ቀን ዐውደ ርእይ ተካሄደ።
ዐውደ ርእዩን መርቀው የከፈቱት የፊኒሽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተለያዩ ባህል ተጠሪ ቄስ ቴሙ ቶኦይቪነን ፣ ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ አንተነህ ጉደታ በኦስሎ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም አስተዳዳሪ ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ለማ በሱፍቃድ ነበሩ ። እንዲሁም ቄስ ሚካኤል ሰንድቪስት ከቲኩሪላ ፊኒሽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣ ሚስተር ቬሪኮቨ ሌፍ የሄልሲንኪ ከተማ አስተዳደር የአስተዳደር ክፍል የበላይ ሃላፊ፣ አቶ ኤልያስ ሳቦሬ በፊንላንድ የኢትዮጲያ ኮንስላር በክብር እንግድነተ ተገኝተዋል ።
በዚህ በፊንሽኛና በአማርኛ ቋንቋ በቀረበው ዐውደ ርእዩ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጥንት ዘመናት፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በውጪ ሀገራት መስፋፋት፣በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አመሠራረት ሂደት፣የቤተክርስቲያኒቷ የወደፊት ትኩረት አቅጣጫ የሚያሳይ ገለጻና ትንታኔ ቀርቧል።

ከዝግጅቱ ማጠቃላይ ላይም  ቄስ ቴሙ ቶኦይቪነን ቤተክርስቲያኗ የምታደርገውን እንቅስቃሴ አድንቀው ፣ ለቤተ ክርስቲያኗ ያመጡትን ማስታወሻ ለደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ለማ በሱፍቃድ አበርክተዋል።

ከዐውደ ርእዩ በኋላ አንዳንድ ታዳሚዎች በሰጡት አስተያየት በቀረበው ዝግጅት መደሰታቸውንና ስለ ቤተክርስቲያኗ የበለጠ እንደተረዱና ወደፊትም እንዲህ ያሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች መቀጠል እንደሚኖርባቸው ጠቁመዋል። ለዐውደ ርእዩም አዘጋጆች ምስጋና አቅርበዋል። በዕለቱም የዐውደ ርዕዩ አርማ የታተመበትን ቲ-ሸርት ለሽያጭ የቀረበ ሲሆን ገቢውም ቤተ ክርስቲያኗን ማጠናከሪያ እንደሚውል ተገልጿል።

ግንቦት 12 ዐውደ ርእይ

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *