ለሁለት ቀናት የቆየ መንፈሳዊ ጉባኤ በሄልሲንኪ ተካሄደ

ለሁለት ቀናት የቆየ መንፈሳዊ ጉባኤ በሄልሲንኪ ተካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በማኅበረ ቅዱሳን አውሮጳ ማዕከል የፊንላንድ ግንኙነት ጣቢያ አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት የቆየው መንፈሳዊ ጉባዔ ባለፈው ሳምንት በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ልዩ ጉባኤ ተካሄዷል ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር መጋቤ ሐዲስ በሙሉ አስፋው መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርትን ጨምረው በንስሐ ሕይወት እና በሥርዓተ ቤተክርስቲያን ዙሪያ ሰፋ ያለ ትምህርት ሰጥተዋል ።

ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ የማኅበረቅዱሳን በአዉሮፖ ማዕከል የፊንላንድ ግንኙነት ጣቢያ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ መንፈሳዊ መዝሙሮች እና ሥነጽሑፍ በደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ቀርቧል ።

በርካታ ምእመናን በተገኙበት በዚህ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ ከኢትዮጵያ ለመጡት መምህር መጋቤ ሐዲስ በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

የደብሩ አስተዳደሪ አያይዘውም በቀጣይ ተመሳሳይ መንፈሳዊ ጉባኤዎች መዘጋጀታቸውን ጠቅሰው በሀገረ ስብከት ደረጃ በአውሮጳ የስካንድርቪያ አገሮች የሚሳተፉበት ስዊድን ጉተንበርግ ከሐምሌ 19 /2011 ዓ.ም ጅምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ከቅዱስ ገብርኤል በዓል ጋር ተያይዞ መዘጋጀቱን እና መምህራንን ከኢትዮጵያ እንደሚመጡ አስታውሰው ምእመናን በጉባኤው ተገኝተው ቃለ እግዚአብሔር ን ይማሩ ዘንድ አሳስበዋል ።

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *