24
Sep 2016
በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ የመስቀል ደመራን በዓል በሄልሲንኪ ከተማ የዮሐንስ ቤ/ክ አጠገብ በሚገኘው (korkeavuorenkatu 12) አደባባይ/ሜዳ/ ሰኞ መስከረም 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ከ17፡30– 20፡30 ፣ የደመራ ሥነ ሥርዓት በማከናወን እንደሚያከብር ተገለጸ። የደመራ ሥነ ሥርዓቱ የደብሩ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ መዘምራን፣ ሕጻናት፣ በሄልሲንኪና አጎራባች ከተሞች የሚገኙ ምእመናን፤ ተጋባዥ ካህናት፣ ዲያቆናት ፣ የፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሓላፊዎች ፣ የከተማው ከንቲባ ጽ/ቤት እና ልዩ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት እንደሚከናወን ታውቋል፡፡ የመስቀል ደመራ በዓል የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአይሁድ አማካኝነት ተቀብሮ ከነበረበት ቦታ የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት የሆነቸው ንግሥት ዕሌኒ ፣ ደመራ......
Read More