Daily Archives: March 11, 2023


11
Mar 2023

በፊንላንድ ዩቫስኲላ ከተማ የቅዱስ ዑራኤል ጽዋዕ ማኅበር ተመሠረተ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እየተገለገሉ የሚገኙ በዩቫስኲላ ከተማ የሚኖሩ ምእመናን መጋቢት ፪/፳፻፲፭ ዓ.ም በቅዱስ ዑራኤል ስም የጽዋዕ ማኅበር መሠረቱ። በዝርወቱ ዓለም የሚኖሩ ምእመናን በየወሩ እየተሰበሰቡ በጋራ በአንድነት በቅዱሳን ስም የጽዋዕ ማኅበር መሥርተው ይጸልያሉ ፣ይማጸናሉ አመቺ በሆነ ጊዜም ቅዳሴ ይቀደስላቸዋል ፣ በዚሁ መሠረት በፊንላንድ ዩቫስኲላ ከተማ የሚገኙ ምእመናን እጣ በመጣል በተደጋጋሚ ቅዱስ ዑራኤል በመውጣቱ በመልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ስም የጽዋዕ ማኅበር ተመሥርቷል ። በዕለቱ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ......

Read More