ልዩ የሕፃናትና አዳጊ የልደት በዓል ፕሮግራም

Olunkylan Vanha kirko Siltavoudintie 12, Helsinki

+++   በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ”ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው” መዝ. 126(127)፥3   ውድ ምዕመናን እና ምዕመናት:- በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና አዳጊ ንዑስ ክፍል የጌታችን እና የመድኃኒታችንን ልደት ምክንያት በማድረግ የፊታችን እሁድ ልዩ የሕፃናትና አዳጊ ፕሮግራም ስላዘጋጀ ሕፃናት በሙሉ ፕሮግራሙን እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። በዕለቱ - ሕጻናት መዝሙር ስነጽሑፍ ያቀርባሉ - ለሁሉም ሕጻናት ስጦታ ይሰጣል - በሕጻናት ዙሪያ ትምህርት እና ወንጌል ይኖራል   በዚህ ቀን ሁላችሁ ምዕመናን እና ምዕመናት እንዲሁም ወላጆች ልጆቻችሁን ይዛችሁ በአድነት ሆነን እግዚአብሔርን እንድናመሰግን በዓሉንም እንድናከብ ጥሪ እናስተላልፋለን።   እሑድ ታኀሣሥ 30 2009 ዓ.ም (January 8, 2017) ሰዓት ቀን 10:00 – ምሽት12:00 (16:00-18:00) ቦታ Siltavoudintie 12, 00640 Helsinki መልካም በዓለ ልደት ይሁንልን!!!     በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና አዳጊ ንዑስ ክፍል ፊንላንድ