Ongoing

የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በዓለ ልደት የክብረ በዓል

Maunulan kirkko Metsäpurontie 15, Helsinki

+ + + በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል፥ አንደበቱም ፍርድን ይንልገራል።"መዝ፦36፥ 30 የክብረ በዓል ጥሪ የተከበራችሁ በፊንላንድና በአጎራባች ሀገሮች የምትገኙ አድባራት አበው ካህናት ወዲያቆናት፥የሰንበት ት/ቤት መዘምራን ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ !የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በዓለ ልደት ታኅሣሥ 22/04/2009 /Des 31.12.2016. ከዋዜማው ዐርብ ጀምሮ በታላቅ ድምቀት ይከበራል። በመሆኑም በዕለቱ ተገኝታችሁ ከጻድቁ በረከት ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ቀን ፡-21-23/04/2009 ዓ.ም (30-31/12/2016) ሰዓት ፡-ዐርብ ምሽት 4:30 – ቅዳሜ ቀን 12:00 (Fri 22:30- Sat 12:00) ቦታ ፡- Kristuksen taivaaseenastumisen kirkko (Läntinen Valkoisenlähteentie 48, Vantaa) ዝርዝር መርሃግብር ዐርብ ማታ በ21/04/2009 ከ22፥30 -01፥00 ፣ገድለ ተክለሃይማኖት ይተረጎማል ትምህርትና መዝሙር ከ01፥00-6፥00 ማኅሌት ይቆማል ከ6፥00-6፥30 ጸሎተ ኪዳን ይደርሳል ከ6፥30-9፥00 ቅዳሴ ይከናወናል ከ9፥00-10፥00 ትምህርትና መዝሙር ከ10፥00-11፥30 ታቦተ ሕጉ ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ዑደት ያደርጋል 12፥00 ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል ከ12፥00-13 መስተንግዶ ተከናውኖ የበዓሉ ፍጻሜ ይሆናል። ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን! በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ፊንላንድ