Loading Events
  • This event has passed.

የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በዓለ ልደት የክብረ በዓል

+ + +
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል፥ አንደበቱም ፍርድን ይንልገራል።”መዝ፦36፥ 30

የክብረ በዓል ጥሪ
የተከበራችሁ በፊንላንድና በአጎራባች ሀገሮች የምትገኙ አድባራት አበው ካህናት ወዲያቆናት፥የሰንበት ት/ቤት መዘምራን ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ !የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በዓለ ልደት ታኅሣሥ 22/04/2009 /Des 31.12.2016. ከዋዜማው ዐርብ ጀምሮ በታላቅ ድምቀት ይከበራል። በመሆኑም በዕለቱ ተገኝታችሁ ከጻድቁ በረከት ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ቀን ፡-21-23/04/2009 ዓ.ም (30-31/12/2016)
ሰዓት ፡-ዐርብ ምሽት 4:30 – ቅዳሜ ቀን 12:00 (Fri 22:30- Sat 12:00)
ቦታ ፡- Kristuksen taivaaseenastumisen kirkko
(Läntinen Valkoisenlähteentie 48, Vantaa)

ዝርዝር መርሃግብር
ዐርብ ማታ በ21/04/2009
ከ22፥30 -01፥00 ፣ገድለ ተክለሃይማኖት ይተረጎማል ትምህርትና መዝሙር
ከ01፥00-6፥00 ማኅሌት ይቆማል
ከ6፥00-6፥30 ጸሎተ ኪዳን ይደርሳል
ከ6፥30-9፥00 ቅዳሴ ይከናወናል
ከ9፥00-10፥00 ትምህርትና መዝሙር
ከ10፥00-11፥30 ታቦተ ሕጉ ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ዑደት ያደርጋል
12፥00 ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል
ከ12፥00-13 መስተንግዶ ተከናውኖ የበዓሉ ፍጻሜ ይሆናል።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!

በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት
የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን
ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት
ፊንላንድ

Start

December 30, 2016 @ 22:30

End

December 31, 2016 @ 13:00

Website

https://www.facebook.com/events/104057150098165/

Location

Maunulan kirkko
Metsäpurontie 15
Helsinki, 00630 Finland

Organizer

የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
Phone
+358 40 684 2226
Email
debreaminoffice@gmail.com
View Organizer Website

Share this Event

REGISTER FOR THIS EVENT