26
Aug 2016
በፊላንድ ሄልሲንኪ አሉንኩላን ቤተክርስቲያን የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ እረፍታቸውን አስመልክቶ የዋዜማ ጉባኤ የደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ ፤ ተጋባዥ እንግዶች መምህር ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ(ከስዊድን) ሊቀ መዘምራን ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ(ከኢትዮጵያ) መምህር ፍቃዱ ሣህሌ(ከኢትዮጵያ) ፣ የሰንበት ት/ቤቱ መዘምህራን እና ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ መንፈሳዊ ስነ-ስርዓት ተከብሯል፡፡ ሕጻናትም በፕሮግራሙ ላይ ዝማሬን አቅርበዋል። በነገውም ዕለት ከቀኑ 12:00 ሰዓት እስከ 18:00 ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 22:00 ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ የአዳር መንፈሳዊ አገልግሎቶች በሶፊያ የባህል አዳራሽ እንደሚቀጥልም ተገልጾዋል። በዋዜማ ሌሊቱን በማህሌት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን በጋራ በመሆን መንፈሳዊ አገልግሎት ይቀጥላል።...
Read More