ልዩ የልደትና የጥምቀት በዓል መርሃ ግብር በሕፃናትና አዳጊ ልጆች

Kotikirkko Adarash Unioninkatu 39, Helsinki

+++   በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ”ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው” መዝ. 126(127)፥3   ውድ ምዕመናን እና ምዕመናት:- በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና አዳጊ ንዑስ ክፍል የጌታችን እና የመድኃኒታችንን ልደት ምክንያት በማድረግ በዚህ ዕለት እሁድ ልዩ የሕፃናትና አዳጊ መርሃ ግብር ስላዘጋጀ ሕፃናት በሙሉ ፕሮግራሙን እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። በዕለቱ - ሕጻናት መዝሙር ስነጽሑፍ ያቀርባሉ - ለሁሉም ሕጻናት ስጦታ ይሰጣል - በሕጻናት ዙሪያ ትምህርት እና ወንጌል ይኖራል   በዚህ ቀን ሁላችሁ ምዕመናን እና ምዕመናት እንዲሁም ወላጆች ልጆቻችሁን ይዛችሁ በአድነት ሆነን እግዚአብሔርን እንድናመሰግን በዓሉንም እንድናከብ ጥሪ እናስተላልፋለን።   እሑድ ጥር 20 2010 ዓ.ም (January 28, 2018) ሰዓት ቀን 9:00 – ምሽት12:00 (15:00-18:00) ቦታ Siltavoudintie 12, 00640 Helsinki መልካም በዓለ ልደት ይሁንልን!!!     በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት የሕፃናትና አዳጊ ንዑስ ክፍል ፊንላንድ