የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል

Maunulan kirkko Metsäpurontie 15, Helsinki

† † † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። "በጨለማ የነበረ ሕዝብ ብርሃንን አየ"ኢሳ ፱፥፪   የተወደዳችሁ ምእመናን ወምእመናት:- የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ ፳፱ የሚከበረውን የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ መርሃግብር ከሌሊት ቅዳሴ ጋር አዘጋጅተናል። በዚህ ቀን በአድነት ሆነን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።   የዕለቱ ዝርዝር መርሃ ግብር እንደሚከተለው ነው፥ ከ22፥00-23፥00 ስብሐተ እግዚአብሔር ይደርሳል። ከ23፥00-23፥30 በዓሉን በተመለከተ በደብሩ መዘምራን ወረብ ይቀርባል። ከ23፥30-00፥00 ጸሎተ ኪዳን ይደርሳል ከ00፥00-02፥30 ቅዳሴ ይከናወናል። ከ03፥00-05፥00 መስተንግዶ ተከናውኖ የበዓሉ ፍጻሜ ይሆናል።   ቀን ፡- ዐርብ ታህሳስ 28 ቀን 2009 ዓ.ም.(Friday January 6 2017) ሰዓት፡- ከምሽቱ 4:00 – ሌሊት 11:00 (22:00 -05:00) ቦታ ፦ Kristuksen taivaaseenastumisen kirkko (Läntinen Valkoisenlähteentie 48)   መልካም በዓለ ልደት ይሁንልን!!!   በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ፊንላንድ