ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን

የእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን መገለጫዎች

የእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን መገለጫዎች

በቀሲስ ብርሃኑ ጎበና ቤት የሚለው ቃል ወገን፤ ነገድ፤ ዘር፤ ትውልድ፤ ጉባኤ፤ ማኅበር ማለት እንደሆነ አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ላይ ጠቅሰዋል፡፡(ኪ.ወ.ክ ገጽ 268) የያዕቆብ ወገን ቤተ ያዕቆብ (ቤተ እስራኤል)፤የዳዊት ወገን ቤተ ዳዊት እንዲባል በመንፈሳዊና በምሥጥራዊ ልደት ከክርስቶስ የተወለዱ ምእመናንም ቤተ ክርስቲያን ይባላሉ፤ ቤተ ክርስቶስ (የክርስቶስ ወገን) እንደ ማለት ነው፡፡ ዳሩ ግን በዘመናችን ስምና ግብር ለየቅል ሆነው በተቃራኒ ያሉት ወገኖች ሳይቀሩ ስሙን መጠሪያ አድርገው አናስተውላለን፤ ዘመናችን አማናዊቱ ቤተ ክርስቲያን ስምዋን ወስደው በሚጠሩ አስመሳዮች የተወረረችበት ወቅት በመሆኑ እውነተኛዋን ለይቶ ማወቅ ግድ ይላል፡፡ እንዲት ቤተ ክርስቲያንን ቤተ ክርስቲያን ዘክርስቶስ የሚያሰኛት በ381 ዓ.ም በቁስጥንጥንያ የተሰበሰቡት 150 ኤጲስ ቆጶሳት (ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን) በቀኖና ሃይማኖታቸው ላይ እንደገለጡት አንዲት(one ) ቅድስት (Holy) የሁሉና በሁሉ ያለች(universal ) እና ሐዋርያዊ ውርስ (Apostolic succession) ያላት ስትሆን ብቻ ነው ከእነዚህ ከአራቱ አንዱን ያጎደለች የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ልትሆን አትችልም አይደለችምም፡፡ እንደ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አመሥጥሮ...


ዝርዝር ንባብ

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን

እግዚአብሔር አምላክ ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ሲያመጣው ከተፈጠረበት ሥርዓት ጋር ነው። የዓለም ተፈጥሮም ያለ ሥርዓት ትርጉም የለውም። ፍጥረት ሁሉ እግዚአብሔርን ከሚያደንቅበት ነገር አንዱ የተሰጠውን ሥርዓት ጠብቆ መጓዙ ነው። ወንዞች ወደ ዝቅተኛ ስፍራ ይፈስሳሉ፣ አራዊት በሌሊት ይወጣሉ፣ ሰዎች ተግባራቸውን በቀን ያከናውናሉ፣ ፀሐይ በምሥራቅ ትወጣለች። ይህ ሁሉ የሚያስተምረን ሥርዓት ከጥንተ ፍጥረት ጀምሮ የነበረና ወደፊትም የሚቀጥል መሆኑን ነው። መዝ ፩፻፫፡ ፮-፳፭። ሥርዓት ሠርዐ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ስም ነው። ትርጉሙም ደምብ አሠራር ማለት ነው። ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም ስንል የቤተ ክርስቲያን መገልገያ ደንብ ማለታችን ነው። አምልኮተ እግዚአብሔር የሚከናወንባት ቤተ ክርስቲያን ምስጢራዊና መንፈሳዊ ሥርዓት አላት። መንፈሳዊ አገልግሎቷንም የምትፈጽምበት ደንብ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ይባላል። ይህም ደንብ የቤተ ክርስቲያን አባቶች በየጊዜው በሲኖዶስ በመወሰን ለቤተ ክርስቲያን ያስረከቡት ነው። በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ የዕለት ተዕለት ሥርዓተ አምልኮታቸውን በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመመራት ያከናውናሉ። በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አማካኝነት ከሚከናወኑት ውስጥ አንዱ...


ዝርዝር ንባብ

error: Alert: Content is protected !!