የልማት ክፍል

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

የደብረ አሜን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስትያን የልማት ክፍል  ቤተክርስቲያናችን ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ዓመታዊ እቅዶችን በማቀድ የደብሩን የገንዘብ አቅም ለማጎልበት የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናል።

ከሚያከናውናቸው ተግባራት መሓከልም:

  • የመንፈሳዊ ጉዞ
  • የንዋየ ቅዱሳት መሸጫ ስቁን በማደራጀት አገልግሎት መስጠት
  • የጸሎት መፃሕፍት፣የህፃናት መፃሕፍት፣የተለያዩ ቅዱሳን ስእላት፣የአንገት መስቀል፣እጣንና ጥዋፍ፣የሕፃናት እና ያዋቂ ነጠላ በመሸጥ ለቤተክርስቲያኑ ገቢ ማስገኘት፡፡
  • የምግብ እና ለስላሳ መጠጦች ሽያጭ በቫንታ ከተማ ግንቦት ወር ላይ በሚዘጋጀው የሰንፌስቲቫል ላይ የሚያቀርብ ሲሆን በተጨማሪም ለልደት፣ለሰርግና ለመሳሰሉት ዝግጅቶች በተመጣጣኝ ዋጋ የምግብ ዝግጅት አገልግሎት ይሰጣል።
  • በዓመት ሦስት ጊዜ የሎተሪ ሽያጭ በማድረግ እና ሌሎች ክንውኖች በማድረግ የቤተክርስቲያናችንን የገንዘብ አቅም ለማሳደግ ጥረት ያደርጋል፡፡

አብዛኛው የእዚህ ክፍል አገልግሎት በእንስት እህቶቻችንና እናቶቻችን የሚከወን ሲሆን፣ የክፍሉ አገልግሎት መጠናከርም በቀጣይ የደብራችንን አገልግሎት ለማስፋፋት ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ። እግዚአብሔር የአገልግሎት ጊዜያቸውን ይባርክልን።

ስብሓት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።

 

ደብረ አሜን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ልማት ክፍል