ስለሕንጻ አስሪ/ግዢ ኮሚቴ ዝርዝር መረጃ

           በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ ማቴ 16፤19

ቤተ ክርስቲያናችን ከተመሰረተች እና ከዚያ በፊት በማኅበር ደረጃ በነበረችበት ወቅት አግልግሎት የምናገኝበት ቋሚ ቦታ ባለመኖሩ ምክንያት እኛ ምእመናን የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በቂ መጠን ለማግኘት አልቻልንም። የደብራችን የምእመናን ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ቢሆንም ይህ መሰረታዊ ችግር እስከ አሁን አልተፈታም። ችግሩን ከመሰረቱ ለመቅረፍ የራሳችን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ሊኖረን ግድ ይላል። በዚህ መሰረት የካቲት 13 /2008 ዓ.ም በምእመናን ምልዓተ ጉባኤ አምስት አባላት ያሉት የሕንጻ አሰሪ/ግዢ ኮሚቴ ተመርጦ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

የእዚህ ኮሚቴ ዋና አላማ የእራሳችን የሆነ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን እንዲኖረን ማኅበረ ምእምኑን በመስተባበር መስራት ነው። ይህንንም አላማ ለማሳካት በየጊዜው የተግባር እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል። ከምእመናን የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ከምእምናን እና ከሰበካ ጉባኤ ጋር በመተባባር በትጋት ይሰራል። በሥራ ሂደት የሚያጋጥሙ መሰናክሎችን ለማለፍ ከምእመናን ሀሳብ እና አስተያየት ይሰበስባል። በየጊዜው ኮሚቴው የደረሰበትን ውጤት ለምእመናን ያሳውቃል።

ኮሚቴው ከተመረጠ በኋላ ስራውን የጀመረው ለእያንዳንድ የኮሚቴ አባላት ዝርዝር ሀላፊነት እና የስራ ድርሻ በማዘጋጀት ነው። በየአመቱ አመታዊ እቅድ በማዘጋጀት እና በማጸደቅ ስራውን ሲያከናውን ቆይቷል። ለከሚቴው ከተሰጠው አብይ ስራ በተጨማሪ፤ በየጊዜው የሚያጋጥሙ የአገልግሎት ቦታ ችግርን ለመፍታት ከሰበካ ጉባኤ ጋር በመሆን ስፊ እንቅስቃሴ አድርጓል።

ከሰባካ ጉባኤ ጋር በመነጋገር ቃለ አዋዲውን መሰረት በመድረግ በ2009 ዓ.ም መግቢያ ላይ ኮሚቴው የራሱ የሆነ ለቤተ ክርስቲያን ማሰሪያ/ግዢ ብቻ የሚንቀሳቀስ የባንክ ሒሳብ ቁጥር ከፍቶ ለምእመናን አስውቋል። ምእመናንም የገንዘብ አስተዋጽዋቸውን ማበርከት ጀምረዋል።  ይህም የባንክ ሒሳብ ቁጥር ከዚህ ጽሁፍ መደምደሚያ ላይ ማገኝት ይቻላል።

የራሳችን ህንጻ ቤተ ክርስቲያን ቢኖረን የሚከተሉት መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አግልግሎቶች በሰፊው ማግኘት እንችላለን።

  • መንፈሳዊ ሕይወታችን እንድን በረታ ቅዱስ ወንጌል በሰፊው እንማራለን።
  • ቅዳሴ መርሃ ግብር በየሳምንቱ እና ከዚያም በላይ ይኖረናል።
  • ልጆቻችን በሃይማኖትና ፣ በምግባር ፣ ታንጸው እንዲያድጉ የሕይማኖት ትምህርት በበቂ ሁኔታ ለማስተማር ያስችለናል።
  • ህጻናት እና አዳጊ ልጆች ባህላቸውን እና ቋንቋቸውን በተገቢው መጠን አውቀው እንዲያድጉ ማስተማሪያ ቦታ እናገኛለን።
  • ወጣቶች አዳጊ ህጻናት በሰንበት ት/ቤት ታቅፈው በሐይማኖት በስነምግባር ታንጸው አንዲያድጉ እና ወደፊትም ቤተ ክርስቲያናችንን እንዲያገለግሉ ይሆናሉ።
  • እናቶችና እህቶች መንፈሳዊና ማህበራዊ ምክክር እንዲያደርጉ ሰፊ እድል ይፈጥራል።
  • በማኅበራዊ ሕይወታችንም ለመረዳዳት ሐዘንችንንም ሆነ ደስታችንን በጋራ ለማሳለፊ እንደ መሰበሰቢያ ሆነ ያገለግለናል።
  • በተለያየ ምክንያት ችግር ወይም ጭንቀት ሲገጥመን ከመንፈሳዊ መምህራን እና አባቶች ምክር በቀላሉ ለማግኘት ያግዘናል።

ከላይ የተዘረዘሩትን ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ማግኘት እንችል ዘንድ ቋሚ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን መግዛት/ መሥራት ጥያቄ የሌለው ወሳኝ ጉዳይ ነው። ይህን ህልማችንን እውን ለማድረግ የእያንዳንዳችን በጎ አስተዋጽኦ በጣም ወሳኝ መሆኑን በመረዳት ፣ በእኔነት ስሜት ተሳትፎ ማድረግ ይኖርብናል።

ይህን ቅዱስ አላማ ለማሳካት ከእኛ ከምእመናን ምን ይጠበቃል? ከሁሉ በላይ በሆነው እግዚአብሔር በሰጠን ትልቅ መንፈሳዊ መሳሪያ ፣ ጸሎት ኮሜቴውን እና የኮሚቴውን ስራ ማሰብ ይገባናል። ለእኛ ከባድ የሚመስል ቢሆንም በእግዚአብሔር ሁሉ ይቻላል እና ይህ ህልማች እውን ሆኖ ለማየት ያብቃን። ስለዚህ እርሶዎም የዚህ ቅዱስ አላማ ተሰተፊ እንዲሆኑ ቤበተ ክርስቲያን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በጋር ሆነን እንደ አንድ ሆነን ከሰራን ይህን ማሳካት ከባድ አይሆንም። ለሥራችን አስፈላጊ የሆነውን ገንዘብ የማሰባሰብ ሂደት ከላይ እንደ ተጠቀሰው  ማሰባሰብ ተጀምሯል። ለእዚህም እንዲረዳን የቃል ማስገቢያ ፎርም ያዘጋጀን ሲሆን፤ ፎርሙን በወረቀት ወይም በኢንተርኔት መሙላት እንችላለን። የፎርሙን ማስፈንጠሪያ(ሊንክ) ከእዚህ ጽሑፍ በታች ማግኘት ይቻላል።

ሐሳቦቻችሁን ለሕንፃ አሰሪ ግዢ ኮሚቴ ለማድረስ ኢሜል መላክ፣  በአካል ለማንኛውም የኮሚቴ አባል መንገር ወይም በስልክ መደወል እንድምትችሉ በታላቅ አክብሮት እና ትህትና እንገልጻለን። የገንዘብ አስተዋጽኦ ለማበርከት ደግሞ ከስር የተገለጸውን  ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት / ለመሥራት ብቻ የሚውለውን ዝግ የባንክ ሂሳብ ቁጥር መጠቀም ይቻላል። በጥሬ ገንዘብ አስተዋጽኦ ለማበርከት የምንሻ ከሆነ ደግሞ በቅዳሴ እና በጉባኤ መርሀ ግብራት ላይ ሒሳብ ተቀባይ ያዘጋጀን ሰለሆነ በደረሰኝ ገቢ ማድረግ ይቻላል።

የቃል ማስገቢያ ፎርም ሊንክ፡  https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdsJijeXpbmhZ5ofUEbULRTxpd3m0Lp5BKO_C0m7cGrPqzQKQ/viewform

ኢሜል አድራሻችን : hintsa.teklehaymanot@gmail.com

ስልክ ቁጥር ፡ 0405751516

የባንክ ሂሳብ ቁጥር(Account number) ፡ FI2181469710254086, DABAFIHH

Beneficiary: Helsingin Debre Amin Abune Tekla Haymanot

Dansken Bank

በረከተ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!