+++
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
“የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል፥ አንደበቱም ፍርድን ይናገራል።” መዝ. 36፥ 30
የተከበራችሁ በፊንላንድና በአጎራባች ሀገሮች አድባራት የምትገኙ አበው ካህናት ወዲያቆናት፥ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ!
የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በዓለ ልደት ታኅሣሥ 21/04/2010 /Dec 30.12.2017. ከዋዜማው ዐርብ ጀምሮ በታላቅ ድምቀት ይከበራል በመሆኑም በዕለቱ ተገኝታችሁ ከጻድቁ በረከት ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ዝርዝር መርሃግብር
ከ22፥00 – 01፥00 ገድል ትርጉምና ስብሐተ እግዚአብሔር ይደርሳል (ዐርብ ማታ በ20/04/2010)
ከ01፥00 – 06፥00 ማኅሌት ይቆማል
ከ 06፥00 – 06፥30 ጸሎተ ኪዳን ይደርሳል
ከ06፥30 – 09፥00 ቅዳሴ ይከናወናል
ከ09፥00 – 10፥00 ትምህርትና መዝሙር
ከ10፥00 – 10፥20 ታቦተ ሕጉ ዑደት ያደርጋል
ከ10፥20 – 10፥40 የደብሩ መዘምራን ወረብ ያቀርባሉ
ከ10፥40 – 11፥30 ማስታወቂያዎችና መልእክቶች
12፥00 ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል
ቦታ፡ Kristuksen taivaaseenastumisen kirkko (Läntinen Valkoisenlähteentie 48, Vantaa)
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት
የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን።