Loading Events
  • This event has passed.

ከ7 ዓመት በላይ ለሆኑ ልጆች በስካይፕ ትምህርት

+++
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ሕዝቤ ሆይ፥ ና ወደ ቤትህም ግባ፥ ደጅህን በኋላህ ዝጋ ቍጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸሸግ። ኢሳ. ፳፮፥፳

ሰላም የክርስቶስ ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ? እንደሚታወቀው ዓለምን እያስጨነቀ ያለው የኮሮና ቫይረስ የዓለም መነጋገሪያ ርዕስ ከሆነ ሰንብቷል። የፊንላንድ መንግሥትም ከ10 ሰው በላይ በአካል ሕዝብ መሰባሰብ እንደማይቻል አዋጅ አውጇል። በዚህ መሠረት በቤተ ክርስቲያናችንም መደበኛ መርሃ ግብር ማድረግ ስለማይቻል ሁላችንም በያለንበት እግዚአብሔርን በጸሎት እንጠይቅ እያልን፤ በደብራችን የወላጆች ኮሚቴ ከ7 ዓመት በላይ ለሆኑ አዳጊ ልጆች እሑድ እሑድ ጠዋት ከ10:00 – 11:00 ሰዓት ድረስ በስካይፕ ትምህርት መዘጋጀቱን ለማሳወቅ እንወዳለን። ስለሆነም ከ7 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች ያላችሁ ወላጆች ልጆቻችሁ በዚህ የስካይፕ አድራሻ https://join.skype.com/jKOE59Q4QxQO በመግባት ትምህርቱን እንዲከታተሉ ታደርጉ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።

ለመርሃ ግብሩ መሳካት ተሳታፊዎች በሰዓቱ እንድትገቡ ትብብራችሁን እንጠይቃለን። ምናልባት በተላከው ሊንክ መግባት ካልቻላችሁ በዚህ ስልክ ቁጥር 0456987878 በመደወል መጠየቅ ትችላላችሁ።

ትምህርቱ በዚህ ሳምንት እሑድ መጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም (22.3.2020) በተጠቀሰው ሰዓት የሚጀመር መሆኑን እናሳውቃለን።

ቀን : ዘወትር እሑድ

ሰዓት : ጠዋት ከ10:00 – 11:00 ሰዓት (በ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ጠዋት ከ 4 :00-5:00 ሰዓት)

የስካይፕ አድራሻ : https://join.skype.com/jKOE59Q4QxQO

ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና አለ። ዘጸ. ፲፭፥፳፮

እግዚአብሔር በአገልግሎት ያበርታን።

በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በስዊድን እና ስካንዲኔቪያን ሀገረ ስብከት
የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ጽጌ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት
የሕፃናትና አዳጊ ንዑስ ክፍል
ፊንላንድ

Date

April 5, 2020

Time

10:00 - 11:00

Location

Online Skype sermon for kids
https://join.skype.com/jKOE59Q4QxQO

Website

View Venue Website

Organizer

የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
Phone
+358 40 684 2226
Email
debreaminoffice@gmail.com
View Organizer Website

Share this Event

REGISTER FOR THIS EVENT