በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው ፤ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል። እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል። መዝ ፴፫፤፲፱
በዓለ ፍልሰተ አጽሙ ለአቡነ ተክለሃይማኖት በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ግንቦት ፲፮ – ፲፯ / May 24 – 25 በታላቅ ድምቀት ይከበራል። በመሆኑም በነዚህ እለታት ተገኝታችሁ ከጻድቁ በረከት ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ተጠርታችኋል።
የበዓሉ ዝርዝር መርሓግብር እንደሚከተለው ቀርቧል።
22:00 – 01:00 ገድል ይተረጎማል ፣ እንዲሁም ስብከተ ወንጌል ከአዲስ አበባ በመጡ መምህር ይሰጣል።
01:00 – 05:00 ሥርዓተ ማኅሌቱ በሊቀ ጠበብት ተክሌ ሲራክ እየተመራ ከተለያዩ አድባራት በሚመጡ ሊቃውንት ይከናወናል።
05:00 – 05:30 ጸሎተ ኪዳን ይደርሳል።
05:30 – 08:00 ጸሎተ ቅዳሴ ይከናወናል።
08:00 – 08:45 ስብከተ ወንጌል ይሰጣል።
09:00 – 10:00 ታቦተ ሕጉ ዑደት ያደርጋል።
10:00 – 10:20 በደብሩ መዘምራን ወረብ ይቀርባል።
10:20 – 10:40 ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል።
10:40 – 11:00 መስተንግዶ ተከናውኖ የበዓሉ ፍጻሜ ይሆናል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት