Loading Events
  • This event has passed.

የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል

† † †

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
“ከየአገሩም ሁሉ እሰበስባችኋለሁ። ወደ ገዛ። ምድራችሁም አመጣችኋለሁ ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ ።” ሕዝ.36፥25

የተከበራችሁ ምእመናንና ምእመናት!
የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል የቅዳሜ ጥር 12 በታላቅ ድምቀት ይከበራል። በዚህ ታላቅ በዓል ላይ እርስዎም ከቤተሰብዎ ጋር እንዲገኙና የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ዝርዝር ፕሮግራም
7:00 – 8:00 ሰዓት ስብሐተ እግዚአብሔር ይደርሳል
8:00 – 10:30 ጸሎተ ቅዳሴ ይከናወናል
10:00 – 10:40 ጥምቀተ ባሕሩ ተባርኮ ሕዝበ ክርስቲያኑ ይረጫል
10:40 – 11:05 ዕለቱን በተመለከተ ወረብ በደብሩ መዘምራን ይቀርባል
11:05 – 11:30 ትምህርት
11:30 – 12:00 መስተንግዶ ተከናውኖ የበዓሉ ፍጻሜ ይሆናል

ቀን ፦ ቅዳሜ ጥር 12 ቀን 2010 ( Sat Jan 20 2018 )
ሰዓት፦ ጠዋት 12:00 – ቀኑ 6:00 ( 6:00 – 12:00 )
ቦታ ፦ Kristuksen taivaaseenastumisen kirkko
(Läntinen Valkoisenlähteentie 48)

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!

በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት
የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን
ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት
ፊንላንድ

Date

January 20, 2018

Time

06:00 - 12:00

Location

Maunulan kirkko
Metsäpurontie 15
Helsinki, 00630 Finland

Organizer

የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
Phone
+358 40 684 2226
Email
debreaminoffice@gmail.com
View Organizer Website

Share this Event

REGISTER FOR THIS EVENT