“በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።” ኤፌሶን 4፥3
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፣
የተከበራችሁ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት አጥቢያ የምትገኙ የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ልጆች ሆይ!
በሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት ዓመታት እና ከዚያ በፉት በአጋጠመው ጠርነት ፣ እና በመሳሰሉት ነባራዊ ሁኔታዎች የተነሳ በአንዲት እናት ቤተ ክርስቲያን ልጆች መካከል የሻከረ መንፈስ ይስተዋላል።
በመሆኑም የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በሄልሲንኪ እና አካባቢው ያላችሁ የተዋሕዶ ልጆች የተለያዩ ቅሬታዎች ያላችሁ ሁላችሁም እኛ የአንዲት እናት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ነንና የሚሰማችሁን ቅሬታ ሁሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከልብ በይቅርታ ፈትተን በአንድ ልብ በአንድ መንፈስ ሆነን መጪውን ዐቢይ ጾም ለመጾም እንድንችል ልዩ መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል። እነሆ ሁላችሁም ከታች በተጠቀሰው ዕለት እንድትገኙ በታላቅ አክብሮት እናት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ለልጆች ታቀርባለች ።
እሑድ የካቲት 12/2015 Feb 19/2023
ሰዓት 13:30 -18:00
የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
ፊንላንድ