በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
የተወደዳቹ የ እግዚአብሔር ቤተሰቦች ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ። እንደሚታወቀው በአሁን ወቅት በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በመንኖርበት ሀገር ከ 10 ሰው በላይ መሰብሰብ የሚከለክል ሕግ ወጥቷል። በመሆኑም የቤተክርስቲያናችንን አገልግሎት በርቀት ስርጭት እንድናደርግ ተገደናል።
የፊታችን ቅዳሜ ቁጥራቸው ከ10 የሚያንስ ካህናት እና ዲያቆናት እንዲሁም የቀረጻ ባለሙያዎች ብቻ የሚገኙበት የ ኪዳን እና የምህላ ጸሎት መርሐግብር በቀጥታ ስርጭት Helsinki Debre Amin Abune Tekle Haymanot Church በሚለው የፌስቡክ ገጻችን በቀጥታ የሚተላለፍ በመሆኑ ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን በሰዓቱ በየቤታችሁ ሆናችሁ እንድትከታተሉ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች ።
ቀን : 04 / April / 2020
ሰዓት : ከጠዋቱ 7:00 – 8:30 ሰዓት
ቦታ : Helsinki Debre Amin Abune Tekle Haymanot Church Facebook page
https://www.facebook.com/eotcHelsinkiTekleHaymanot
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን
መረጃና ግንኙነት ክፍል