+ + +
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
“የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው” ምሳሌ ፲፥፯
የተከበራችሁ ምእመናንና ምእመናት
የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት በረከታቸዉ ይደርብንና በየወሩ የምናከብረዉ የዝክራቸዉ መርሐ ግብር የፊታችን ሰኞ ሚያዚያ ፳፬ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም ይሆናል። መርሐ ግብሩ የዝክር መርሐ ግብር ብቻ ነው፤ ስለዚህ ብዙ ጊዜ ስለማይወስድ ከበረከቱ ለመሳተፍ እንድንገናኝ ቤተክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።
ቀን ፦ ሰኞ ሚያዚያ ፳፬ ቀን ፳፻፰ (Monday May 2 2016)
ሰዓት፡ 18:00 – 19:00ቦታ፦ Pyhittäjä Aleksanteri Syväriläisen kappeli Myllypurontie 1, Helsinki
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት
የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን
ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት
ፊንላንድ