የሄልሲን ደብረ አሚን አቡነ የተክለሃይማኖት ደብር በፊላንድ መንግስት እውቅና አገኘ!

by ግንኙነት ክፍል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር በፊላንድ መንግስት በቤተክርስቲያን ደረጃ ተመዝግቦ እውቅና መሰጠቱን የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ አስታወቁ።
የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ደብር በማኅበር ደረጃ ከ20 አመታት በላይ ማስቆጥሩ ይታወሳል፤ ይሁንና ላለፉት 5 ዓመት በቤተክርስቲያን ደረጃ ተመዝግቦ በፊንላንድ መንግሥት ዘንድ እውቅና ለማግኘት ከፍተኛ ጥረቶች መደረጋቸውን ተገልፇል።
እንደ ደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ለማ ገለፃ የተደረጉት ጥረቶች በመጨረሻ ተሳክተው በፊንላንድ ሀገር የመጀመሪያው በሀገሪቱ መንግስት ዘንድ እውቅና የተሰጠው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ተብሎ መመዝገቡን ተናገረዋል።
በቀጣይነትም የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የራሱ የሆነ ሕንፃ (ቤተ ክርስቲያን) ይኖረው ዘንድ ኮሚቴ ተዋቅሮ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑ ቀሲስ ለማ ጨምረው ገልፀዋል።
Recommended Posts
በፊንላንድ ዩቫስኲላ ከተማ የቅዱስ ዑራኤል ጽዋዕ ማኅበር ተመሠረተ።
March 11, 2023
እግዚአብሔረ የተመሰገነ ይሁን
Egziabeher yimesegen Qesis Lemma ye abune tekelehayimanot tekl bego abat bertuln