በፊንላንድ ዩቫስኲላ ከተማ የቅዱስ ዑራኤል ጽዋዕ ማኅበር ተመሠረተ።

በፊንላንድ ዩቫስኲላ ከተማ የቅዱስ ዑራኤል ጽዋዕ ማኅበር ተመሠረተ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እየተገለገሉ የሚገኙ በዩቫስኲላ ከተማ የሚኖሩ ምእመናን መጋቢት ፪/፳፻፲፭ ዓ.ም በቅዱስ ዑራኤል ስም የጽዋዕ ማኅበር መሠረቱ። በዝርወቱ ዓለም የሚኖሩ ምእመናን በየወሩ እየተሰበሰቡ በጋራ በአንድነት በቅዱሳን ስም የጽዋዕ ማኅበር መሥርተው ይጸልያሉ ፣ይማጸናሉ አመቺ በሆነ ጊዜም ቅዳሴ ይቀደስላቸዋል ፣ በዚሁ መሠረት በፊንላንድ ዩቫስኲላ ከተማ የሚገኙ ምእመናን እጣ በመጣል በተደጋጋሚ ቅዱስ ዑራኤል በመውጣቱ በመልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ስም የጽዋዕ ማኅበር ተመሥርቷል ።


በዕለቱ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድም በቦታው ተገኝተዋል ።
ዩቫስኲላ ከሄልሲንኪ ወደ 300 ያህል ኪሎ ሜትር ርቃ የምትገኝ ከተማ ናት ።
የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስትያን በቀጣይም በተለያዩ ከተሞች ሁለትም ሦስትም ሆነው የሚኖሩትን ምእመናንን የመጎብኘትና መንፈሳዊ አገልግሎቷን ተደራሽ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን ከደብሩ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *