በበረዶዋማ ፊንላንድ አገር የጥምቀት በዓል በድምቀት ተከበረ

የስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን፣ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሰሱ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በርካታ ምእመናን በተገኘበት በድምቀት ተከብሯል።
የበዓሉ ሥነ ሥርዓት የስዊድን፣ ስካንዲናቪያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በሆኑት በመልአከ አሚን የተመራ ሲሆን፤ በዓሉን የተመለከ ትምህርት ከኢትዮጵያ በመጡት በዲያቆን ታደሰ ወርቁ ትምህርት ተሰጥቷል። በፊንላንድ ተወልደው ያደጉ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት የጽጌ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ተተኪ መዘምራንም በዓሉን የሚያዘክረውን ያሬዳዊ መዝሙር አቅርበዋል።

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *