ለ፫ተኛ ጊዜ ቅብዓ ሜሮን የማፍላት ሥርዓተ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ እየተከናወነ ይገኛል

ለ፫ተኛ ጊዜ ቅብዓ ሜሮን የማፍላት ሥርዓተ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ እየተከናወነ ይገኛል

በመ/ር አቤል አሰፋ

(ኢኦተቤ ቴቪ ጥቅምት ፳፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ)

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅብዓ ሜሮን የማፍላት የጸሎት መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
ቀድሞ ከግብፅ ተዘጋጅቶ ይመጣ የነበረው ቅብዓ ሜሮን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲዘጋጅ ይህ ለ፫ ተኛ ጊዜ ነው።

ማለዳ ጠዋት ፲ ሰዓት በተጀመረው ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ; ምእመናንና ካህናት ለ፯ ተከታታይ ቀናት በጸሎት እንዲተባበሩ ቀደም ብሎ በቅዱስነታቸው ጥሪ ቀርቧል። ይህንኑ አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ባስተላለፉት መልዕክት ቅብዓ ሜሮን ዝግጅቱን ተከትሎ በሀገራችን እየደረሰ ላለው መከራ እንዲያበቃ የጸሎት አዋጅ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ መታወጁን ገልጠዋል። ገዳማትና አድባራቱ በሙሉ በጸሎት እንዲተባበሩም ጥሪ አቅርበዋል።

ቤተክርስቲያናችን ለሚጠመቁ ምዕመናንን በቅብዓ ሜሮን አማካኝነት ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ታሳድራለች። ተጠማቂው ቅብዓተ ሜሮን በመቀባት መንፈስ ቅዱስ ያድርበታል። የቃል ኪዳኑ ታቦት (ፅላት) ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በመንበረ ክብሩ ላይ በመቀመጥ አገልግሎት እንዲሰጥ አስቀድሞ በዚህ በተቀደሰ ቅብዓ ሜሮን ተባርኮ መሰየም አለበት ። ቤተ ክርስቲያን ከታነጸ በኋላ ፤ በውስጡ ሙሉ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከመስጠቱ በፊት በቅብዓተ ሜሮን መባረክ አለበት። ሥርዓቱ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት ከጥቅምት ፳፩ እስከ ፳፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ድረስ ይከናወናል።

EOTC TV

++++++++++++++++++++++++++++++++
የወቅታዊ መረጃ ከትክክለኛው ከቅድስት ቤተክርስቲያን ልሳን ለማግኘት ተከታዮን የዩቲዩብ የፌስ ቡክ ቴሌግራም እና ኢንስታግራም ሊንኮች በመጫን ሰብስክራይብ እና ላይክ ያድርጉ፡፡ ሌሎችም ሰብስክራይብ እንዲያደርጉ በማድረግ መንፈሳዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ፡፡
የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv

የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel

የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel

የቲክ ቶክ ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *