የአገልግሎት ምስጋና መርሐ ግብር ተዘጋጀ

by ግንኙነት ክፍል
በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለወ/ሮ አለማች ገብረ ሚካኤል የአገልግሎት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጠ።
በሀገረ ፊንላንድ ከሦስት ዐሥርት ዓመታት በላይ በመንፈሳዊ አገልግሎት በማኅበራዊ አገልግሎት ለሚታውቁት ወ/ሮ አለማች ፣ ሐምሌ ፲፯/፳፻፲፫ ዓ.ም በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት የምስጋና መርሐ ግብር ተዘጋጀ ።
የምስጋና ዝግጅት የምስክር ወረቀት ስነ-ሥረዓት
በዕለቱም በመርሐግብሩ የታደሙት ምእመናን ወ/ሮ አለማች በሀገረ ፊንላንድ በስደት ለሚገኙት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ያዘነውን በማጽናናት ፣ በመጠየቅ የሀገረ ፊንላንድንም ሥርዓተ ሀገሩንም በማለማመድ ከፍተኛ አገልግሎት ማበርከታቸውን ተናግረዋል ። ወ/ሮ አለማች በተለይ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ከታላቁ ካህን አባታቸውና ከለጋሷ እናታቸው የወረሱትን በጎ ተግባር ስደቱ ተጽእኖ ሳይፈጥርባቸው ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን ኢትዮጵያ በጎ ባህላቸው ሳይበረዝ እስከ ዛሬ ድረስ የቆዩ ጠንካራ የሚነበብ መጽሐፍ የሆኑ እናት መሆናቸው በተሳታፊዎቹ ተገልጧል።
ወ/ሮ አለማች የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስትያን ሲመሠረትም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ብቻ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያኗ ከተመሠረተች በኋላም እስከ ዛሬ ድረስ በሁሉም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያለምንም መሰልቸት እያገለግሉ መሆናቸው በምሳሌነት የተገለጠ ሲሆን ፣ ወ/ሮ አለማችም ከእድገታቸው ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን የሕይወታቸውን ተመክሮ ለታዳሚው ሕዝብ አጋርተዋል ።
በዕለቱ በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ እንደተናገሩት ፣ወ/ሮ አለማች በመንፈሳዊ ሕይወት ፣ እንዲሁም በዝርወት ዓለም ከባድ የሆነውን የማኅበራዊ ኑሮን ፣ እንዲህም በስደት ወደ ፊንላንድ የሚመጡትን ኢትዮጵያንን በማማከር በተለይ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተም በኋላ ከፍተኛ አገልግሎት ማበርከታቸውን ተናግረው ይህንን የወ/ሮ አለማችን በጎ ተግባር የሚከተል ተተኪ ትውልድ ያስፈልጋል ብለዋል።
በመጨረሻም ለዚሁ በጎ መርሐግብር በተለያዩ ተግባራት የተሳተፉትን የአጥቢያውን ምእመናንን ሁሉ አመስግነው ወደፊትም በዚሁ መልክ የሚያገለግሎትን የአጥቢያውን ምእመናን የአገልግሎትን ምስጋና መርሐ ግብር እንደሚዘጋጅ ተናግረዋል ።
የምስጋና ዝግጅቱ በፎቶ
Recommended Posts

ማኅሌተ ጽጌ ወደ ፊንላንድኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ተመረቀ
October 04, 2023

ሀገረ ስብከቱ የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸም ጠቅላላ ጉባኤውን አጠናቀቀ
September 03, 2023

በፊንላንድ ሀገር የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቡራኬ ተከናወነ !
September 03, 2023