ትምህርተ ሃይማኖት

አዲሱ ዓመት (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)

አዲሱ ዓመት (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)

አዲሱ ዓመት ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላምና የጤና እንዲኾንላችሁ ትሻላችሁን? እንኪያስ ገና ከጅመሩ በስካር፣ በዘፈን፣ በገቢረ ኀጢአት ለማሳለፍ አታቅዱ፡፡ የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይኾን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኀጢአት አትጀምሩት፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፣ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚኾኑት በተፈጥሮአቸው እንደዚያ ኾነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲኾን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማክሰኞ ከዘንድሮ ማክሰኞ የተለየ አይደለም፡፡ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው፡፡ የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኀጢአት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመትም ክፉና መከራ የመላበት ይኾንብናል፡፡ አዲሱን ዓመት በበጐ ሥራ የምንጀምረው ከኾነ በዓመቱ በምናደርገው ማንኛውም ክንውን ላይ በጐ ተጽዕኖ ያሳድርብናል፡፡ በትግሃ ሌሊት፣ በቀዊም፣ በጾም በጸሎት እንድንበረታ ስንቅ ይኾነናል፡፡ በስካር፣ በዘፈን፣ በኀዘን የምንጀምረው ከኾነ ግን ዓመቱ ሙሉ እንዲህ የተጐሳቈለ ዓመትን እናሳልፋለን፡፡ ሕይወታችንን በከንቱ እንገፋለን፡፡...


ዝርዝር ንባብ

መልካም ጓደኛ

መልካም ጓደኛ.pdf መልካም ጓደኛ  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን በዚህ በምንኖርበት አለም ይብዛም ይነስም አንድ ወይም ከዚያ በላይ ጓደኛ ይኖረናል። በእርግጥ በዚህ ጽሁፍ ዉስጥ ለመግለጽ የተፈለገዉ የወንድ ወይም የሴትን የተቃራኒ ፆታ የፍቅር ጓደኝነትን ሳይሆን መልካም የልብ ጓደኛ ማለት ምን ማለት ነዉ? የሚለዉን ለማየት ሲሆን ምናልባትም ብዙዎቻችን በተለምዶ እገሌ እኮ የእገሌ የልብ ጓደኛዉ ነዉ፤ እገሊትም ለእገሊት የልብ ጓደኛዋ ናት ስንልም እንሰማለን። በአንጻሩ ደግሞ አንዳንድ ሰዎች እገሌ ወይም እገሊት እኮ ጓደኛ አይወጣለትም ወይም አይወጣላትም እንዲያዉ ምክንያቱ ምን ይሆን? በማለት አስተያየት እንሰጣለን። ይሁን እንጅ የልብ ጓደኛ ብለን ስንናገር መለኪያችን ከምን አንጻር እንደሆነ መገንዘቡ የበለጠ የመልካም ጓደኛን ትርጉም እንድንረዳ ይረዳናል። ምክንያቱም ብዙ ሰዎች ጓደኛ የሚመርጡበትን መመዘኛ ካለማወቅ የተነሳ እንዲሁ ራሳቸዉ በቀመሩት የጓደኝነት መመዘኛ ቀመር አኳያ ብቻ ስለሚሆን በሆነ አጋጣሚ ካስቀመጡት ቀመር በተቃራኒ ኢምንት በሆነና እዚህ ግባ በማይባል ምክንያት በመካከላቸዉ የግጭት ፀሐይ ሲገባ የሚፈጠረዉ እሳትና ትርምስ...


ዝርዝር ንባብ

ልደተ ክርስቶስ (ገና)

ልደተ ክርስቶስ (ገና)

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ!!! ከጌታችን ከልደቱ ያገኘነው ምንድን ነው? ዳግም ልደት በአዳም በደል ምክንያት አጥተነው የነበረው ልጅነታችንን ክርስቶስ በልደቱ ዳግመኛ እንደመለሰልን ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ “ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።” ዮሐ 1፥12 በማለት ገልጾታል። ሰላም በጌታችን ልደት ለዓለም ሁሉ የሚሆን ዘላለማዊ ሰላም ተገኝቷል። ይህም “ክብር እግዚአብሔር በሰማያት ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጐ ፈቃድ” እያሉ ቅዱሳን መላእክት በመዘመራቸው ተረጋግጧል። ሉቃ 2፥14። ስለዚህ በክርስቶስ ያገኘነው እውነተኛ ሰላም በእኛ ጸንቶ እንዲኖር ዘወትር በጾምና በጸሎት እየተጋን ስለሰላም የምንማፀን ሆነን ልንገኝ ይገባል። ሰላም የክርስትና መታወቂያ አርማ ነውና። ብርሃን “በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃንን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።” ኢሳ 9፥2። ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ያህል በዲያብሎስ ቁራኝነት ተይዞ የነበረው አዳም ወደሚደነቀው ብርሃን የተሸጋገረው በክርስቶስ ልደት ነው። እኛም በልደቱ ያገኘነውን የጽድቅ ብርሃን ጠብቀን ለመኖር (ብርሃነ ወንጌልን) ፈጽመን ከኃጢአት ርቀን...


ዝርዝር ንባብ

ጾመ ፍልሰታ

ጾመ ፍልሰታ

ጾመ ፍልሰታ ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጉም ስናነሣ ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የወጣ /የተገኘ/ ሲሆን በጥሬ ትርጉሙ ከምድር ከመቃብር መለየት፣ ማረግ፤ ወደ ላይ መውጣት የሚለውን ትርጉም ያመለክታል፡፡ በዚህ መሠረት ጾመ ፍልሰታ በአጠቃላይ የእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋዋን ከመቃብር መለየትና ወደ ገነት ማረጉን የሚያመለክት ሲሆን ቅድስት ቤተክርስቲያን ምዕመናን እንዲጾሙት ከምታዘው ሰባቱ አጽዋማት አንዱና ለዓመቱ ደግሞ የመጨረሻው ጾም ነው፡፡  ይህ ጾመ ፍልሰታ በሌላ አጠራር ጾመ ማርያምም በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ ወቅት በብዛት የሚወሳው /የሚነገረው/ ቃለ እግዚአብሔር በአብዛኛው ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የተያያዘ በመሆኑና የእርስዋ የሥጋዋ ፍልሰት መታሰቢያ በመሆኑ ጾመ ማርያም ተባለ፡፡ ነገር ከስሩ ውኃ ከጥሩ እንዲሉ አበው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ይህንን የእመቤታችንን ጾም ለምን እንደምታከብር ለመዘርዘር እንወዳለን፡፡ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህች የሰው ልጆች መኖሪያ በሆነችዋ ምድር ከእናቷ ማህፀንና ከአባቷ አብራክ ተከፍላ ከተወለደችበት ጊዜ አንስቶ እስከ መጨረሻዋ የዕረፍት ዘመን በምድር ላይ ስልሳ አራት ዓመታትን ማለትም ከእናት ከአባቷ ቤት ሦስት ዓመት ከሰባት ወር፣ በቤተመቅደስ 12ዓመት፣ በቤተ ዮሴፍ 34ዓመት ከሦስት ወር፣ ከጌታ ዕርገት በኋላ ከወንጌላዊው ዮሐንስ ጋር 14ዓመት ኖራለች፡፡ ከዚህ በኋላ...


ዝርዝር ንባብ