Loading Events
  • This event has passed.

የቅዳሴ መርሐ-ግብር

+ + +

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ውድ ምዕመናን እና ምዕመናት:-
በኮሮና ቫይረስ(Covid-19) ወረርሽኝ ምክንያት ቤተ ክርስቲያናችን ዝግ ሆና መቆየቷ የሚታወቅ ነው። ይሁን እንጂ ከjune 1 ቀን 2020 ዓ.ም ጀምሮ የእምነት ተቋማት ተከፍተው እስከ 50 ሰው በቤተ ክርስቲያን መሰብሰብ እንዲችሉ ከፊንላንድ መንግስትና የህብረተሰ ጤና ኢንስቲትዩት መመሪያ ከቅድመ ጥንቃቄ ጋር ተሰጥቷል። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ እየሰራ ነው። በመሆኑም በአሁን ሰዓት ቤተ ክርስቲያናችን በከፊል አገልግሎት የምትሰጥ መሆኑን በደስታ እየገለጽን የተሟላ አገልግሎት እስኪጀመር እና የመንግስትን አዋጅ ሙሉ በሙሉ መተግበር እስክንችል ድረስ ክርስትና ለሚያስነሱ እና ለአዳዲስ(ለመጀመሪያ ጊዜ) የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን ለሚቀበሉ ምዕመናን ቅድሚያ ተሰቶ ምዝገባ በመመዝገብ አገልግሎት መሳተፍ እንደምትችሉ ከወዲሁ ማስገንዘብ እንወዳለን።
ከላይ የተጠቀሱት ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ከመምጣታቸው በፊት ከፊንላንድ መንግስት የተሰጡትን አዋጆች እና ምክረ ሀሳቦች ማማላት ይኖርባቸዋል። ከነዚህም ውስጥ፡

  1. ማንኛውም ምእመን ሳይመዘገቡ እና የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደሩን አውንታዊ ምላሽ ሳያገኙ በስተቀር ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣት የተከለከለ ነው።
  2. የህመም ምልክቶች (የራስ ምታት፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ በተደጋጋሚ ማስነጠስ) ከታዩ ወደ ቤ/ክ መምጣት የተከለከለ ነው።
  3. በጤና ባለሞያ ወይም በመንግስት ለ14 ቀን ከቤት እንዳይወጡ(quarantine) ወይም ለብቻዎ እንዲገለሉ (isolation) ከተነገርዎት ወደ ቤተ ክርስቲያን መመጣት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
  4. የስኳር፣ የልብ፣ የአስም፣ የደም እና የመሳሰሉ ህመምተኞች ለበሽታው ተጋላጭ የመሆን እድሎ ስለሚጨምር ወደ ቤ/ክ እንዲመጡ አይመከርም።
  5. ቤ/ክ ምግብ ይዞ መምጣት እና በሕብረት መመገብ የተከለከለ ነው።
  6. በሳል እና በማስነጠስ ጊዜ በመሐረብ/በሶፍት ወረቀት ካልሆነው በክርኖት አፍ እና አፍንጫዎ በሸፈን ይኖርቦታል።

እግዚአብሔር አምላክ ፈቅዶ ቤተ ክርስቲያናችን መደበኛ አገልግሎት እስክትጀምር ድረስ እንደተለመደው የቀጥታ ስርጭት በቤተ ክርስትያናችን ፌስ ቡክ እና ዩትዩብ (Facbook & Youtube) የምናስተላልፍ መሆኑን እያሳሰብን ከፊንላንድ መንግስት እና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚሰጡትን አዋጆች እና መመርያዎች እየተከታተልን የምናሳውቃችሁ መሆኑንም ከወዲሁ እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፣ ሳይመዘገቡና ተራዎ ሳይደርስዎ መምጣት በጥብቅ የተከለከለ ነው።

እግዚአብሔር አምላክ አገራችንን፣ ህዝቦችዋን እና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን።

በስዊድንና ስካንዲናቪያ ሀገሮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት
የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት
ፊንላንድ

Date

October 19, 2020

Time

06:30

Website

http://www.teklehaymanot.fi

Location

Kristuksen taivaaseenastumisen kirkko
Läntinen Valkoisenlähteentie 48
Vantaa, 01300 Finland

Organizer

የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
Phone
+358 40 684 2226
Email
debreaminoffice@gmail.com
View Organizer Website

Share this Event

REGISTER FOR THIS EVENT