Uncategorized


01
Nov 2022

በመ/ር አቤል አሰፋ (ኢኦተቤ ቴቪ ጥቅምት ፳፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ) በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅብዓ ሜሮን የማፍላት የጸሎት መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል። ቀድሞ ከግብፅ ተዘጋጅቶ ይመጣ የነበረው ቅብዓ ሜሮን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲዘጋጅ ይህ ለ፫ ተኛ ጊዜ ነው። ማለዳ ጠዋት ፲ ሰዓት በተጀመረው ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ; ምእመናንና ካህናት ለ፯ ተከታታይ ቀናት በጸሎት እንዲተባበሩ ቀደም ብሎ በቅዱስነታቸው ጥሪ ቀርቧል። ይህንኑ አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ......

Read More


21
Aug 2022
የደብረ ታቦር በዓል በሄልሲንኪ በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከበረ

በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የደብረ ታቦር በዓል የደብሩ ሕጻናት አዳጊ ልጆች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል ። የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይሜኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ በበዓሉ ላይ እንደተናገሩት በተለይ በዝርወቱ ዓለም ተወልደው የሚያድጉ ተተኪው ትውልድ የበዓላትን አከባበር እንዲሁም ትውፊታዊውንም ቅብብል በተግባር ያውቁ ዘንድ እንዲያስችል ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። ወላጆችም ለዚሁ ትልቅ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ ብለዋል ። በቀጣይ የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ አዲስ ዓመትም እንዲሁ በደሜቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚከበር ጠቁመዋል። በተያያዘ ዜና ነሐሴ 14 /2014 ዓ.ም በታምፔሬ ከተማ በታምፔሬ የሚገኙ የቅድስት ኪዳነ ምሕረት ጽዋዕ ማኅበር አባላት......

Read More


26
Dec 2020

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስዊድንና ስካንድኔቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ቤተክርስቲያን እሑድ ታኅሣሥ 11 ቀን /2013 (20.12.2020) በርቀት በስካይፔ ባካሄደው ዓመታዊ የአጥቢያ ምእመናን መንፈሳዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፈረንጆቹ ከ2021 ዓ.ም ጀምሮ በደብሩ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ቤተክርስቲያኗን የሚያገለግሉ አዲስ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላ ምርጫን አካሄዷል። ጠቅላላ ጉባኤውን በጸሎት ክፍተው የመሩት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ የዕለቱን አጀንዳዎች ማለትም  የደብሩን የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ነጥቦች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ  የ2021 በጀት ዓመት ማጽደቅ  የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ማከናወን መሆናቸውን ገልጠዋል ። የጠቅላላ ጉባኤ የምርጫው......

Read More


29
Aug 2019
በዓለ እረፍቱ ለአቡነ ተክለሃይማኖት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ተከበረ

በስዊድንና እካንድናቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በዓለ እረፍቱ ለአቡነ ተክለሃይማኖት ነሐሴ 18 እና 19/2011 ዓ.ም በድማቅ ሥነ ሥርዓት ተከበረ። በበዓሉ ላይ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የተገኙ ሲሆን ሌሎችም ከ አውሮጳ ከተለያዩ አድባራት የተጋበዙ ሊቃውንትም በበዓሉ ተገኝተዋል ። ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ከበዓሉ ቀደም ብለው ሄልሲንኪ የገቡ ሲሆን ከፊንላንድ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሊዮ ጋር የፊንላንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርትሲያን ለቤተ ክርስቲያናችን እስካሁን ላደረገችውና እያደረገች ላለው ትብብር አመስግነዋል። ወደፊትም ለአስፈላጊው አገልግሎት ሁሉ እንዲተባበሩ ጥሪ ከማቅረባቸው በተጨማሪም የጋራ በሆኑ አገልግሎቶች ተባብሮ መሥራትን በተመለከተ በማንሳት ውይይት አድርገዋል ።......

Read More


19
Mar 2019
የሀገረ ስብከት ምሥረታ ተከናወነ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን አውሮጳ መንበረ ጵጵስናው ስዊድን ስቶኮሆልም የሆነ ሀገረ ስብከት ተመሠረተ ።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት አሠርተ ዓመታት ያህል በአስተዳደር ተከፍላ ብትቆይም በሐምሌ 2010 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሕደቱ ከተፈጸመ በኋላ በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት አውሮጳን ለዐራት አህጉረ ስብከት እንዲከፈል መወሰኑ ይታወቃል ። በዚህ መሠረት በስዊድንና እስካንድንቢያን ሀገሮች እራሱን ችሎ አንድ ሀገረ ስብከት እንዲሆንና በአንጋፋው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ እንዲመራ በመወሰን የተነሳ መጋቢት 6 እና 7 /2011 ዓ.ም በመንበረ ጵጵስናው ስቶኮሆልም ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ሰብሳቢነት ምሥረታው......

Read More


17
Dec 2018

የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለቀጣይ ሁለት ዓመታትየሚያገለግሉ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት ምርጫ አካሄደ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን  አውሮጳ በስዊድንና አካባቢው ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 7 ቀን 2011 ዓ.ም (16.12.2018 ) ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ከ2019  – 2020 ዓ.ም የሚያገለግሉ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤአባላት ምርጫ አካሄዷል፡፡ለሁለት ዓመታት በሰበካ ጉባኤ አባልነት የሚያገለግሉ አባላትን ለመምረጥ ጥቅምት 24 ቀን 2011 ዓ.ም (3.11.2018) በአጥቢያው ምእመን ሶስት አባላት ያለው የአስመራጭ ኮሚቴ  ተመርጦ የምርጫ ሂደቱን ተከናውኗል። በሐምሌ ወር 2010 ዓ•ም በአስተዳደር ለሁለት ተከፍሎ የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስን አንድነትን ተከትሎ......

Read More


24
Sep 2018
በፊንላንድ ሄልሲንኪ ታላቅ የአንድነት እና ሰላም ጉባኤ ተካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ውስጥ በሚገኘው በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ከመስከረም 12 – 13 ቀን 2011 ዓ.ም ታላቅ የአንድነት እና ሰላም ጉባኤ ተካሄደ። በጉባኤው ላይም የአውሮፓ አኅጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ቀዳማዊ እና ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ፣ ጥሪ የተደረገላቸው ካህናት፤ ከመላው ፊንላንድ የተሰባሰቡ ምዕመናን እና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች  ተገኝተዋል። ጉባኤው ቅዳሜ መስከረም 12 ቀን 2011 ጠዋት በሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት እየተመራ በጸሎተ ቅዳሴ ተጀምሯል። የአንድነት ጉባኤውን ለማድረግ ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያትም በቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር መከፋፈል ምክንያት ለሁለት ተከፍለው የነበሩትን በፊንላንድ የሚኖሩ ምዕመናን......

Read More


09
Sep 2018
አዲሱ ዓመት (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)

አዲሱ ዓመት ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላምና የጤና እንዲኾንላችሁ ትሻላችሁን? እንኪያስ ገና ከጅመሩ በስካር፣ በዘፈን፣ በገቢረ ኀጢአት ለማሳለፍ አታቅዱ፡፡ የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይኾን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኀጢአት አትጀምሩት፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፣ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚኾኑት በተፈጥሮአቸው እንደዚያ ኾነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲኾን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማክሰኞ ከዘንድሮ ማክሰኞ የተለየ አይደለም፡፡ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው፡፡ የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኀጢአት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ......

Read More


30
Jul 2018

የተላኩብፁዓን አባቶች፣የተደረሰበትን ስምምነት የሚያስረዳ መግለጫ ለጉባኤው አቀረቡ፤ የነበረው የአባቶች መለያየት ለውግዘት በሚዳርግ ደረጃ ላይ ደርሶ እንደነበር የታወቀ ነው፤ የተደከመበት ዕርቀ ሰላም ለውጤት በመብቃቱ በስምምነቱ መሠረት ውግዘቱ ተነሥቶአል፤ የጳጉሜ 1984፣ የመስከረም 1985፣ የጥር 1999ዓ.ም.ቃለ ውግዘት፣ከዛሬ ጀምሮ ተነሥቶአል፤ ከልዩነት በፊት የተሾሙ ነባር ሊቃነ ጳጳሳትንና ከልዩነት በኋላ የተሾሙትን ተቀብሏቸዋል፤ ††† ስያሜያቸው እንዳለ እንደተጠበቀ፣በውጭ ሀገርም ኾነ በሀገር ቤት ተመድበው ያገለግላሉ፤ ከ1-6 ተራቁጥር የተዘረዘሩትን የዕርቀ ሰላም ነጥቦች ምልዓተ ጉባኤው ተቀብሎ አጽድቋል፤ የቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና የሀገር ሰላም የበለጠ እንዲጠናከር የበኩሉን ይፈጽማል፤ ጠ/ሚሩ፣ ችግሩ የሀገርም መኾኑን በመገንዘብ አስተጋባኢና አሰባሳቢ መመሪያ ሰጥተዋል፤ ብዙ የተደከመበት ጉዳይ ፈጣን መፍትሔ እንዲያገኝ ስላደረጉ ልባዊ ምስጋና ያቀርባል:: ††† ምንጭ: ሐራ ዘተዋሕዶ...

Read More


29
Jul 2018

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስና ልኡካን አባቶች ረቡዕ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ፤ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ዛሬ መግለጫ ይሰጣሉ በመጪው መስከረም ለመመለስ ቢያስቡም፣ በጠ/ሚሩ ጥሪ አሳጠሩት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአቀባበል ዐቢይ ኮሚቴ ዝግጅቱን እያጣደፈ ነው፤ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ፣ ከ17 በላይ የተሟሉ ማረፊያዎች ተዘጋጁ፤ ይፋዊ የአቀባበል መርሐ ግብሩ፣ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከናወናል፤ “ለመቀበል እየተዘጋጀን ነው፤ታላቅ ደስታ ነው፤”/ብፁዕ ዋና ሥ/አስኪያጁ/ †††   የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶሳዊ አንድነት በአባቶች ዕርቀ ሰላም መመለሱን ተከትሎ፣ ላለፉት 26 ዓመታት በአሜሪካ በስደት የቆዩት 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በመጪው ሳምንት ረቡዕ፣ ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ሀገራቸው......

Read More