የጻድቁ አባታችን በዓለ ዕረፍት ተከብሮ ዋለ

የጻድቁ አባታችን በዓለ ዕረፍት ተከብሮ ዋለ

በሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖትን የበዓለ ዕረፍታቸውን ዓመታዊ ክብረ በዓል ነሐሴ 22 ቀን 2008ዓ.ም. (28.08.16 እ.ኤ.አ) ፣ ቮሳሪ በሚገኘው WP_20160828_017የፊኒሽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሶፊያ ማዕከል በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ፡፡ በበዓሉ ላይ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱ ፈቃድ የደብሩ አስተዳዳሪ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ቀሲስ አንገሶም በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሄልሲንኪ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ እና የደብሩ ዲያቆናትና ቀሳውስት መምህር ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ(ከስዊድን) ፣ ሊቀ መዘምራን ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ(ከኢትዮጵያ)፣ መምህር ፍቃዱ ሣህሌ(ከኢትዮጵያ) ፣ እንዲሁም ካህናት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ ሕጻናትና በፊንላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያና የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን ተገኝተዋል፡፡

የበዓሉ ዋዜማ ምሽት፣ ማኅሌት ከመገባቱ ቀደም ብሎ መንፈሳዊ ትምህርት ሲሰጥ ከቆየ በኋላ፣ የጻድቁን በዓለ ንግሥ የሚያዘክር ስብሐተ እግዚአብሔር በማኅሌታውያን ካህናት የተቆመ ሲሆን ፣ የጻድቁን ዕረፍታቸውን ዜና የሚዘክር ገድለ ተክለሃይማኖትም ተነቧል፡፡ ሥርዐተ ቅዳሴው በቀዳሲያኑ ልዑካን ከተከናወነ በኋላ በሊቀ መዘምራን ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ መዝሙራት የተዘመሩ ሲሆን፣ በመቀጠልም በመምህር ፍቃዱ ሳህሌ ”የቅዱሳን ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው” የሚለውን የዳዊት መዝሙር ቃል መነሻ በማድረግ ሰፋ ያለ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል፡፡
በቤተ መቅደስ የነበረው ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ፣ ታቦተ ሕጉ ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ በካህናት፣ በዲያቆናWP_20160828_035ት ፣ በሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራንና በምእመናን ታጅቦ ዑደት ከተደረገ በኋላ፣ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያሬዳዊ ዜማና ወረብ ቀርቧል ፣ በመቀጠልም የደብሩ ሰንበት ት/ቤት መዘምራን ለዕለቱ ያዘጋጁትን ወረብ ያቀረቡ ሲሆን ፣ በመጨረሻም በሊቀ መዘምራን ቀሲስ ምንዳዬ መዝሙራት ቀርበዋል፡፡
የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በርሱፈቃድ በሰጡት ቡራኬና ቃለ ምዕዳን፤ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የተጋድሎ ሕይወታቸውን ከፈጸሙ በኋላ በበዓለ ዕረፍታቸው ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ታላቅ በዓል መሆኑንና በዚህ ታላቅ በዓል ላይ ተገኝቶ ከጻድቁ በረከት መሳተፍ ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑን ገልጸዋል፣ አያይዘውም በዓሉን የተሳካ ለማድረግ ጥረት ላደረጉ ምእመናንና የአገልግሎት ክፍሎች በሙሉ ምስጋናቸውን በማቅረብ በተለይም ከሌሊት ጀምሮ በአገልግሎት ለተባበሩት በፊንላንድ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካህናትና ዲያቆናት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በታቦተ ህጉ ማረፊያ ቦታ የነበረው አገልግሎት ከተፈጸመ በኋላ ታቦተ ሕጉ በህዝበ ክርስቲያኑ ታጅቦ ወደ መንበረ ክብሩ የተመለሰ ሲሆን በስተመጨረሻም በደብሩ መስተንግዶ ክፍል የምሣ ግብዣ ተደርጎ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡በበዓለ ንግሡ ላይ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ተተኪ ዲያቆናትና የደብሩ ሰንበት ት/ቤት መዘምራን በደብሩ በተዘጋጀውና በተለያዩ ሕብረ – ቀለማት ባጌጠው የደብሩ የክብረ በዓል ልብሰ ተክህኖ እና ጥንግ ድርብ ደምቀው ለክብረ በዓሉ የተለየ ውበት ሰጥተውታል፡፡

የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ ዕረፍት ፣ በየዓመቱ ነሐሴ 24 ቀን ዓመታዊ ክብረ በዓል ሆኖ በተለያዩ ክፍለ ዓለማትና በተለይ በገዳማቸው በደብረ ሊባኖስ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ይውላል፡፡

የጻድቁ አባታችን በዓለ ዕረፍት 2016

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *