ቤተ ክርስቲያኗ ልጆቿ ምእመናን ያሉበትን ሁኔታ የሚከታተል ኮሚቴ ማዋቀሯ ተገለጠ

ቤተ ክርስቲያኗ ልጆቿ ምእመናን  ያሉበትን ሁኔታ የሚከታተል ኮሚቴ ማዋቀሯ ተገለጠ

በስዊድንና እስካንድናቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ዓለምን እያስጨነቀ የሚገኘው በኮረና ቫይረስ እየቀጠፈ ያለው ሕዝብ በዝርወት ከሚከኙት መካከል ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ተጠቃሾች መሆናቸው የሚታወቅ በመሆኑ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት በሥሯ አገልግሎት የሚያገኙትን በመላዋ ፊንላንድ የሚገኙትን ምእመናንን ጤንነት እና አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ የመረዳዳት በጎ ተግባር የሚያስተባብር ኮሚቴ ማዋቀሯን የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ለማ በሱፍቃድ ገለጹ፡፡ ኮሚቴው የአጥቢያው ምእመናን በዚህ ቫይረስ ቢያዙ እንኳን አስፈላጊውን ማኅበራዊ ሥነ ልቡናዊና ተመሳሳይ እገዛዎችን ለማድረግ እንደሚያስተባብር ተጠቁሟል ፡፡ ኮሚቴው ከሄልሲንኪ ውጪ ባሉት ምእመናን ባሉባቸው ከተሞችም የመረዳዳት አገልግሎቱን ተደራሽ የሚያደርግበትን አቅጣጫም ማስቀመጡን ታውቋል፡፡ የደብሩ አስተዳዳሪ እንደገለጡት ይህንን አስጨናቂ ወቅት ምእመናን በመረዳዳት በመተሳሰብ ሆኖ ማሳለፍ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን የምንኖርበትን ሀገር የጤና መመሪያ በተከተለ መልኩ እንዲሆን አሳስበዋል ፡፡በተያያዘ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አባላት በየ ምእመናኑ ዘንድ ስልክ እየደወሉ ጤንነታቸውን በመጠየቅ ላይ እንደሆኑም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በመጨረሻም በደብሩ ለተቋቋመው ኮሚቴ አስፈላጊውን መረጃ በመስጠት በጋራ ይህንን አስከፊ ጊዜ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ እንድናለፈው የሁላችሁም ምእመናን መረዳዳትና መተሳሰብ አስፈጊ መሆኑን አሳስበዋል፡፡

share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *