በፊንላንድ ታምፔሬ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥርዓተ ቅዳሴ ተከናወነ

በፊንላንድ ታምፔሬ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥርዓተ ቅዳሴ ተከናወነ
 በፊላንድ ታምፔሬ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥርዓተ ቅዳሴ ተከናወነ። የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ኪዳነ ምሕረት የጽዋዕ ማኅበር ጥቅምት 1/2012 ዓ ም የተቋቋመ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሜ ነሐሴ 16 ቀን 2012 ዓ.ም ( 22/8/2020 ) Tuomiokirkokatu 27 ላይ በሚገኘው የፊላንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የቅዳሴው አገልግሎት የተመራው  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በስዊድንና ስካንዲናቪያን ሀገሮች ሀገረ ስብከት የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ እንዲሁም በፊላንድ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ደብረ ሰላም መድኅንያዓለም ቤተክርስቲያን ምክትል አስተዳዳሪ  ቀሲስ አንገሶም  ዲያቆናት አማካኝነት የተፈጸመ ሲሆን የሄልሲንኪ ደብረ አሚን ጽጌ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት መዘምራን እንዲሁም ከፊላንድ ከተለያየ ከተማ የመጡ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ምእመናን ተገኝተዋል። በዓሉን ያዘጋጁት  የታምፔሬ ኪዳነ ምሕረት የጽዋዕ ማኅበር አባላት ምእመናን አስተባባሪነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ልዩ በዓል  በሥርዓተ  ቅዳሴ  ተከብሯል። ታምፔሬ ከተማ ከሄልሲንኪ 175  ኪ.ሜ በሰሜን አቅጣጫ የምትገኝ ከተማ ነች በዕለቱም በዚያው ከተማ የተወለዱ  ሁለት ሕጻናት ክርስትና የተነሱ ሲሆን እንዲሁም ከኦሉ ከተማ የመጡ ሙሽሮች በዕለቱ በሥርዓተ ተክሊል ጋብቻቸውን ፈጽመዋል።
ከቅዳሴ በኋላ  በታምፔሬ ኪዳነ ምሕረት የጽዋዕ ማኅበር አባላት አዘጋጅነት  ለምዕመና እና ለሙሽሮቹ  ምሳ ያዘጋጁ ሲሆን በመጨረሻም መልአከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፍቃድና  ቀሲስ አንገሶም ለኪዳነ ምሕረት የጽዋዕ ማኅበር አባላት መሰባሰባቸውን እንዳያቋርጡና እንዲበረቱ  አባታዊ ምክራቸውና ዕለቱ በሚመለከት መንፈሳዊ ትምህርት ከሰጡ በኋላ ይህንን አገልግሎት እንድናከናውን ለረዳን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው እንዲሁም ይህንን አገልግሎት እንዲከናወን ለተራዱ  ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኖል።
share

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *