Large Posts

17
Dec 2018

የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለቀጣይ ሁለት ዓመታትየሚያገለግሉ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት ምርጫ አካሄደ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን  አውሮጳ በስዊድንና አካባቢው ሀገረ ስብከት በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 7 ቀን 2011 ዓ.ም (16.12.2018 ) ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ከ2019  – 2020 ዓ.ም የሚያገለግሉ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤአባላት ምርጫ አካሄዷል፡፡ለሁለት ዓመታት በሰበካ ጉባኤ አባልነት የሚያገለግሉ አባላትን ለመምረጥ ጥቅምት 24 ቀን 2011 ዓ.ም (3.11.2018) በአጥቢያው ምእመን ሶስት አባላት ያለው የአስመራጭ ኮሚቴ  ተመርጦ የምርጫ ሂደቱን ተከናውኗል። በሐምሌ ወር 2010 ዓ•ም በአስተዳደር ለሁለት ተከፍሎ የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስን አንድነትን ተከትሎ......

Read More


24
Sep 2018
በፊንላንድ ሄልሲንኪ ታላቅ የአንድነት እና ሰላም ጉባኤ ተካሄደ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ውስጥ በሚገኘው በፊንላንድ የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ከመስከረም 12 – 13 ቀን 2011 ዓ.ም ታላቅ የአንድነት እና ሰላም ጉባኤ ተካሄደ። በጉባኤው ላይም የአውሮፓ አኅጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ቀዳማዊ እና ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ፣ ጥሪ የተደረገላቸው ካህናት፤ ከመላው ፊንላንድ የተሰባሰቡ ምዕመናን እና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች  ተገኝተዋል። ጉባኤው ቅዳሜ መስከረም 12 ቀን 2011 ጠዋት በሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት እየተመራ በጸሎተ ቅዳሴ ተጀምሯል። የአንድነት ጉባኤውን ለማድረግ ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያትም በቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር መከፋፈል ምክንያት ለሁለት ተከፍለው የነበሩትን በፊንላንድ የሚኖሩ ምዕመናን......

Read More


09
Sep 2018
አዲሱ ዓመት (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)

አዲሱ ዓመት ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላምና የጤና እንዲኾንላችሁ ትሻላችሁን? እንኪያስ ገና ከጅመሩ በስካር፣ በዘፈን፣ በገቢረ ኀጢአት ለማሳለፍ አታቅዱ፡፡ የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይኾን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኀጢአት አትጀምሩት፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፣ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚኾኑት በተፈጥሮአቸው እንደዚያ ኾነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲኾን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማክሰኞ ከዘንድሮ ማክሰኞ የተለየ አይደለም፡፡ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው፡፡ የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኀጢአት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ......

Read More


30
Jul 2018

የተላኩብፁዓን አባቶች፣የተደረሰበትን ስምምነት የሚያስረዳ መግለጫ ለጉባኤው አቀረቡ፤ የነበረው የአባቶች መለያየት ለውግዘት በሚዳርግ ደረጃ ላይ ደርሶ እንደነበር የታወቀ ነው፤ የተደከመበት ዕርቀ ሰላም ለውጤት በመብቃቱ በስምምነቱ መሠረት ውግዘቱ ተነሥቶአል፤ የጳጉሜ 1984፣ የመስከረም 1985፣ የጥር 1999ዓ.ም.ቃለ ውግዘት፣ከዛሬ ጀምሮ ተነሥቶአል፤ ከልዩነት በፊት የተሾሙ ነባር ሊቃነ ጳጳሳትንና ከልዩነት በኋላ የተሾሙትን ተቀብሏቸዋል፤ ††† ስያሜያቸው እንዳለ እንደተጠበቀ፣በውጭ ሀገርም ኾነ በሀገር ቤት ተመድበው ያገለግላሉ፤ ከ1-6 ተራቁጥር የተዘረዘሩትን የዕርቀ ሰላም ነጥቦች ምልዓተ ጉባኤው ተቀብሎ አጽድቋል፤ የቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና የሀገር ሰላም የበለጠ እንዲጠናከር የበኩሉን ይፈጽማል፤ ጠ/ሚሩ፣ ችግሩ የሀገርም መኾኑን በመገንዘብ አስተጋባኢና አሰባሳቢ መመሪያ ሰጥተዋል፤ ብዙ የተደከመበት ጉዳይ ፈጣን መፍትሔ እንዲያገኝ ስላደረጉ ልባዊ ምስጋና ያቀርባል:: ††† ምንጭ: ሐራ ዘተዋሕዶ...

Read More


29
Jul 2018

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስና ልኡካን አባቶች ረቡዕ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ፤ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ዛሬ መግለጫ ይሰጣሉ በመጪው መስከረም ለመመለስ ቢያስቡም፣ በጠ/ሚሩ ጥሪ አሳጠሩት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአቀባበል ዐቢይ ኮሚቴ ዝግጅቱን እያጣደፈ ነው፤ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ፣ ከ17 በላይ የተሟሉ ማረፊያዎች ተዘጋጁ፤ ይፋዊ የአቀባበል መርሐ ግብሩ፣ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከናወናል፤ “ለመቀበል እየተዘጋጀን ነው፤ታላቅ ደስታ ነው፤”/ብፁዕ ዋና ሥ/አስኪያጁ/ †††   የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶሳዊ አንድነት በአባቶች ዕርቀ ሰላም መመለሱን ተከትሎ፣ ላለፉት 26 ዓመታት በአሜሪካ በስደት የቆዩት 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ በመጪው ሳምንት ረቡዕ፣ ሐምሌ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ሀገራቸው......

Read More


27
Jul 2018

ሲኖዶሳዊው የዕርቀ ሰላም ልኡካን አባቶች ስምምነት ዝርዝር: ኹለቱም ቅዱሳን ፓትርያርኮች በእኩል የአባትነት ክብር ያገለግላሉ   አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ በአንድ የቅዱስ ሲኖዶስ አመራር ትመራለች፤ 4ኛው ፓትርያርክ በጸሎት እና በቡራኬ፣ 6ኛው ፓትርያርክ በአስተዳደር ሥራ፤ የኹለቱም ስም፣ቤተ ክርስቲያን ባለችበት ዓለም ሁሉ ዘወትር በጸሎት ይነሣል፤ ሰማዕቱ አቡነ ቴዎፍሎስ ለሞት ከተላለፉበት ጀምሮ የቀኖና ጥሰት ተፈጽሟል፤ ቅ/ሲኖዶስ፣ የቤተ ክርስቲያንን ክብር ባለማስጠበቁ ልጆቿን ይቅርታ ይጠይቃል፤ ††† ጥሰቱን ለመከላከልና ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ፣ቅዱስ ሲኖዶስ ደንብ ያዘጋጃል፤ በኹለቱም ሲኖዶስ የተላለፈው ቃለ ውግዘት፣ በጋራ ምልዓተ ጉባኤ ይፈታል፤ ከልዩነት በኋላ የተሾሙ ቅቡል ናቸው፤አጠራራቸው እንደ ቅደመ ተከተላቸው፤ ለውጭ ቤተ ክርስቲያን፣የየሀገሩን ሕገ መንግሥት ያገናዘበ መመሪያ ይወጣል፤ የስምምነቱን ተግባራዊነትና......

Read More


05
Jul 2018

የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ በሁለቱ ሲኖዶሶች መሓከል የተጀመረውን እርቀ ሰላም እንደሚደግፍ አስታወቀ፡፡ እርቀ ሰላሙን በሚመለከት በወጣው ባለ አምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ ላይ እንደተጠቆመው የሁለቱ ሲኖዶሶች አባቶች እርቀ ሰላሙን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈጽሙ፣ ለእዚህም ሂደት የተቋቋመው አስተባባሪ ኮሚቴ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ደብሩ እንደሚደግፍ ተጠቁሟል፡፡ በተጨማሪም፣ በአጥቢያው እና በውጭ አባቶች አስተዳደር ሥር ያሉ ማኅበረ ምእመናን እንዲሁም ሌሎች ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያን የእርቀ ሰላሙን ሂደት እንዲደግፉ እና ለእርቁ መሳካትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል፡፡  ...

Read More


25
May 2018
ሰባተኛ ዓመት ምሥረታና ፍልሰተ ዐፅሙ ለአቡነ ተክለሃይማኖት በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

ሰባተኛ ዓመት ምሥረታና ፍልሰተ ዐፅሙ ለአቡነ ተክለሃይማኖት በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ በየዓመቱ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው ፍልሰተ ዐፅሙ ለአቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ ክብረ በዓል እና የደብሩ ሰባተኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በዘንድሮ ዓመት በተለየ ሁኔታ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በፊንላንድ  የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ቅዳሜ ግንቦት 11 2010 ዓ.ም ተከብሮ ዋለ :: በዕለቱ ታቦተ አቡነ ተክለሃይማኖት ወደ ፊንላንድ የመጣበት እና ደብሩ እንደ አጥቢያ ቤተክርስቲያን  የተመሠረተበት ሰባተኛ ዓመት “ ሃይማኖታችንን ለልጆቻችን ዛሬ እናስተምር” በሚል መሪ ቃል በፊንላንድ ሄልሲንኪ የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ማእምራን ቀሲስ ዮሴፍ ምክትል አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም ቀሲስ ......

Read More