28
Apr 2016
“አንዱ ስለሁሉ ሞተ” (2ቆሮ 5÷14) የስሞነ ሕማማት ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያናችን ልዩ ቀን ነው፡፡ ይህ ቀን ልዩ ነው፣ የማይታመመው ታሞ የዋለበት፣ የወደቁትን ከተረሱበት ከትቢያ የሚያነሳ እሱ ሲወድቅ ሲነሣ የዋለበት፣ ሕመምተኞችን የሚፈውስ እሱ ሲያቃስት የዋለበት፣ ከሲኦል የዲያብሎስ ግርፋት ነፃ የሚያወጣ ሲገረፍ የዋለበት ወልደ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ድኅነት በመስዋዕትነት ሙሽራ የሆነበት የደስታ ቀን የዓመፃ መዝገባችን መገልበጡ እርግጥ የሆነበት ፣ አሳዳጃችን አሳሪያችን ዲያብሎስ ከነወጥመዱ ድል የተነሳበት ቀን ነውና፣ ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን የተለያየ ምስጢራዊ ስያሜዎች ተሰጥቶታል፡፡ የስቅለት ዓርብ ይባላል የዓለም ሁሉ መድኀኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለዓለም ድኅነት መስዋዕት......
Read More
የፀሎተ ሐሙስ በዓል በቤተክርስቲያናችን ተከብሮ ዋለ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ የሚከናወነው የፀሎተ ሐሙስ የእግር አጠባ እና የጸሎተ ቅዳሴት ሥነ ሥርዓት ዛሬ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ የደቀ...
Read More
ዕለተ ሐሙስ
ይህ ዕለት በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነው፡፡ ሕፅበተ እግር ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ወንጌሉ እንዲህ ይላል ‹‹እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ...
Read More
ሰሙነ ሕማማት ረቡዕ – የምክር ቀን
ለምን የምክር ቀን ተባለ? ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም...
Read More
ሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ የጥያቄ ቀን
በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ ጥያቄውም “በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?” የሚል ነበር፡፡ የካህናት አለቆች ያቀረቡት ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታችን ሰኞ ዕለት...
Read More
ሰሙነ ሕማማት ሰኞ – አንጾሖተ ቤተ መቅደስ እና መርገመ በለስ
በቅዱስ ማርቆስ ወንጌል እንደተገለጠልን ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ በምትባል መንደር ያድርና በማግስቱም ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ተራበ ፡፡/ማር. 11.11-14/ ቅጠል ያላትን በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፣ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ...
Read More
ቤተ ክርስቲያናች በዛሬው ዕለት አዲስ ድረ ገጽ አስመረቀች
የሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክርለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት አዲስ ድረ ገጽ አስመረቀች። በድረ ገጽ ስም www.teklehaymanot.fi በመባል የተሰየመውን ድረ ገጽ መርቀ የከፈቱት የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ብሉይ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ ሲሆኑ የተሠራው ሥራ እጅግ...
Read More
ሆሣዕና ዕለት ከተፈጸሙት ተግባራት ምን እንማራለን?
ፍጹም ትህትናን ነብዩ ኢሳይያስ ”እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር”(ኢሳ 6፥1)። ብሎ የተናገረለት የጌቶች ጌታ የንጉሦች ንጉሥ የሆነ አምላክ ራሱን ዝቅ አድርጎ በአህያ ጀርባ መቀመጡ ፍጹም ትህትናን...
Read More