አመታዊውን የቅዱስ ሚካኤል በአል አስመልክቶ መንፈሳዊ ጉዞ

Turun Ortodoksinen Seurakunta Yliopistonkatu 19 B 3, turku, Finland

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል።” መዝሙር ፴፫ ፡፯ የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች:- እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በቱርኩ የቅዱስ ሚካኤል ጽዋ ማህበር አመታዊውን የቅዱስ ሚካኤል በአል ምክንያት በማድረግ የቅዳሴ መርሃ ግብር እና የአንድ ቀን ጉባኤ አዘጋጅተዋል። እርስዎም በእዚህ ዕለት በቦታው በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች። የጉባኤዉንም መኖር ያልሰሙትን እንድትጠሩልን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። የጉባኤው ዝርዝር ሰአት ከታች ተያይዟል። ቀን፡- ቅዳሜ ሰኔ ፲፩ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. (June 18, 2015) ሰዓት፡- ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ ሰዓት (በኢትዮጵያ አቆጣጠር) ቦታ፦ Yliopistonkatu 19 B 3, 20100 Turku ረድኤተ እግዚአብሄር አይለየን !!! †††